Yetenaweg and Engender Health https://srhr.yetenaweg.com Sexual and Reproductive health and rights (SRHR) in Ethiopia Wed, 06 Mar 2024 14:00:09 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.5.5 https://srhr.yetenaweg.com/wp-content/uploads/2024/01/yetenawegfinallogo-1-150x150.png Yetenaweg and Engender Health https://srhr.yetenaweg.com 32 32 SRHR Training https://srhr.yetenaweg.com/srhr-training/ Sun, 03 Mar 2024 21:17:00 +0000 https://srhr.yetenaweg.com/?p=4430 Yetena Weg and EngenderHealth have partnered to advocate for improved attention to SRHR. Their collaborative efforts aim to raise awareness, engage in policy dialogue, and drive sustainable change. Through digital platforms, they will disseminate SRHR, provide continued professional development for healthcare professionals, and advocate for policies targeting stakeholders. Together, their united endeavors aim to create a lasting impact in the health care system by advancing SRHR and promoting gender equality.

Yetena weg and Engenderhealth have collaborated to provide CME program for selected Trainees.
It’s designed to provide health care professionals with the necessary tools, skills and up to date information to effectively address SRHR issues.

The training aims to empower healthcare providers and improve the quality of SRH care for individuals and the community.

]]>
የወር አበባ ኡደት መዛባት Understanding Menstrual Abnormalities https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%8a%a1%e1%8b%b0%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%8b%9b%e1%89%a3%e1%89%b5-understanding-menstrual-abnormalities/ Wed, 28 Feb 2024 18:42:22 +0000 https://srhr.yetenaweg.com/?p=4393 በዚህ የጤና ወግ መርሃግብር ስለ የወርአበባ መዛባት፣ ተያያዥ ስለሆኑ የጤና አክሎች እና መፍትሄዎቻቸው እንዲሁም መቼ የጤና ባለሞያ ማማከር እንደሚገባን እንወያያለን፡፡ እንግዳችን ዶ/ር ገብረስላሴ አንዱአለም This is a short podcast where we discuss what menstrual irregularities are, their risk factors, when to be concerned, the impact on daily life and it's management. Guest Speaker Dr Gebresilassie Andualem

Listen on Clubhouse Listen on Clubhouse

]]>
የቅድመ እርግዝና ክትትል Pre Conception care https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%89%85%e1%8b%b5%e1%88%98-%e1%8a%a5%e1%88%ad%e1%8c%8d%e1%8b%9d%e1%8a%93-%e1%8a%ad%e1%89%b5%e1%89%b5%e1%88%8d-pre-conception-care/ Wed, 28 Feb 2024 18:32:02 +0000 https://srhr.yetenaweg.com/?p=4390 እሁድ ቀን ስለ ቅድመ እርግዝና ክትትል በሚኖረን ውይይት ላይ ይቀላቀሉን፡፡ ተጋባዥ እንግዳ ዶ/ር ክፍሎም ተስፋዬ Join us on Sunday on our discussion regarding preconception care. Guest Speaker Dr Kiflome Tesfaye

Listen on Clubhouse Listen on Clubhouse

]]>
Family Planning https://srhr.yetenaweg.com/family-planning/ Wed, 28 Feb 2024 18:24:46 +0000 https://srhr.yetenaweg.com/?p=4387 Join us for this informative session about the different family planning options including contraception methods and fertility awareness. With Dr Misikir Anberbir

Listen on Clubhouse Listen on Clubhouse

]]>
Infertility https://srhr.yetenaweg.com/infertility/ Wed, 28 Feb 2024 18:21:06 +0000 https://srhr.yetenaweg.com/?p=4384 Let's talk about it! Join us this Sunday as we talk about infertility and the treatment options available in our country. With Dr Meseret Ansa

Listen on Clubhouse Listen on Clubhouse

]]>
ጾታዊ ጥቃት Gender based Violence https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8c%be%e1%89%b3%e1%8b%8a-%e1%8c%a5%e1%89%83%e1%89%b5-gender-based-violence/ Wed, 28 Feb 2024 18:07:20 +0000 https://srhr.yetenaweg.com/?p=4380 ጾታዊ ጥቃት ከዶ/ር ኑሩ መሀመድ ኡመር ፣ ሜሮን አረጋው እና ሩት ይትባረክ ጋር Gender based Violence with Dr Nuru Mohammed Oumer, Meron Aragaw and Ruth Yitbarek.

Listen on Clubhouse Listen on Clubhouse


]]>
የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር እና ሌሎች የማህጸን ካንሰሮች Cervical Cancer and Other Gynecologic Malignancies https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%88%85%e1%8c%b8%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%8c%ab%e1%8d%8d-%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%88%8c%e1%88%8e%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%88%85/ Wed, 28 Feb 2024 17:33:07 +0000 https://srhr.yetenaweg.com/?p=4363 የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር እና ሌሎች የማህጸን ካንሰሮች ከዶ/ር ዳዊት ወርቁ ካሳ ጋር Cervical and other gynecologic malignancies with Dr Dawit Worku Kassa

Listen on Clubhouse Listen on Clubhouse

]]>
የስነ ተዋልዶ ጤና በኢትዮጵያ Sexual and Reproductive Health https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%88%b5%e1%8a%90-%e1%89%b0%e1%8b%8b%e1%88%8d%e1%8b%b6-%e1%8c%a4%e1%8a%93-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-sexual-and-reproductive-health/ Wed, 28 Feb 2024 17:21:39 +0000 https://srhr.yetenaweg.com/?p=4357 Come join us on SUNDAY to discuss your experience regarding sexual and reproductive health services and learn why Yetena Weg and EngenderHealth partnered to work on Sexual and Reproductive Health Rights.

Listen on Clubhouse Listen on Clubhouse

 

]]>
የአባላዘር በሽታዎች (SEXUALLY TRANSMITTED INFECTIONS) https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%89%a3%e1%88%8b%e1%8b%98%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%bd%e1%89%b3%e1%8b%8e%e1%89%bd-sexually-transmitted-infections/ Sun, 12 Nov 2023 21:52:30 +0000 https://yetenaweg.com/?p=3909 በ- ማህሌት አላምነው ሀይሌ (ሚዮንግሳንግ የህክምና ኮሌጅ -1ኛ አመት (PC1)

አርትኦት እና እርማት – በ ዶ/ር ምስክር አንበርብር (Gynecologist/Obstetrician)

 

የአባላዘር በሽታዎች ምንድን ናቸው?

የአባላዘር በሽታ (SEXUALLY TRANSMITTED INFECTIONS) በዋናነት በወሲብ የሚተላለፉ በሽታዎች ናቸው። የአባላዘር በሽታ ከሰው ወደ ሰው በደም፣ በግንኙነት ጊዜ በሚፈጠሩ ፈሳሾች፣ እንዲሁም ከእናት ወደ ልጅ በእርግዝና ጊዜ ወይም በውልደት ጊዜም ሊተላለፉ ይችላል።

እንደ አለም ጤና ድርጅት ሪፖርት 30 በላይ ባክቴሪያዎች፣ ቫይረሶች፣ እና ጥገኛ ተውሳኮች ለተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች መከሰት ምክንያት ናቸው። የአባላዘር በሽታዎች በአብዛኛው ጊዜ ምልክት አያሳዩም። በዚህም ምክንያት ጤነኛ ተብሎ የሚታሰብ ሰው በቀላሉ በሽታውን ሊያስተላልፍ ይችላል።

 

የአባላዘር በሽታ ምልክቶች ምንድናቸው?

የአባላዘር በሽታዎች በየፊናቸው የተለያዩ ምልክቶች ሊያሳዩም ወይም ላያሳዩም ይችላሉ።

ሊታዩ ከሚችሉ ምልክቶች ወስጥ ከታች የተዘረዘሩት ተጠቃሽ ናቸው፦

  • በብልት እና አካባቢው እብጠት፣ቁስለት እና የህመም ስሜት
  • ሽንት በሚሸናበት ጊዜ ሕመም ወይም የማቃጠል ስሜት
  • ከብልት ያልተለመደ ሽታ እና መልክ ያለው ፈሳሽ ማየት
  • የብልት መድማት
  • በግንኙነት ጊዜ ያልተለመደ የሕመም ስሜት እና
  • ትኩሳት፣ የመሳሰሉት ምልክቶች ተጠቃሽ ናቸው።

የአባላዘር በሽታ ምልክቶች ለበሽታው ከተጋለጡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሊታዩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ለአመታት ከባድ የሚባል ምልክት ሳያሳይ ሊቆይ ይችላል።

የተለያዩ አይነት የአባላዘር በሽታዎች አሉ። ከነዚህም መካከል ጥቂቶቹ  የሚከተሉት ናቸው፦

ጨብጥ (GONORRHEA)

በባክቴሪያ የሚመጣ የአባላዘር በሽታ ነው። ጨብጥ የያዘው ግለሰብ በሽንት ጊዜ የማቃጠል ስሜት ሊያሳይ ይችላል። በተጨማሪም ከብልት ውስጥ ነጭ፣ ቢጫ ወይም አረንጓዴ ፈሻሽ ሊወጣ ይችላል። በአብዛኛው ጊዜ ጨብጥ በሴቶች ላይ ምልክት አያሳይም።

 

ቂጥኝ (SYPHILIS)

ቂጥኝ በባክቴሪያ የሚመጣ የአባላዘር በሽታ ነው። በጊዜ ካልታከመ ከባድ የሆነ የጤና ችግሮችን ያስከትላል። ቂጥኝ የሚተላለፈው  በግንኙነት ጊዜ በሚከሰት ንክኪ ነው።

ቂጥኝ የተለያዩ ደረጃዎች አሉት፦

  1. አንደኛ ደረጃ (PRIMARY SYPHILIS) የቂጥኝ የመጀመሪያ ምልክት በብልት አካባቢ ቁስለት ሲሆን ለበሽታው ከተጋለጡ 3 ሣምንት በኋላ ሊታይ ይችላል። ቁስለቱ የህመም ስሜት የለውም እና በሴቶች ላይ የመደበቅ ባህርይ አለው። 3-6 ሳምንት በኋላ ቁስለቱ በራሱ ይድናል።
  2. ሁለተኛ ደረጃ (SECONDARY SYPHILIS) ቁስለቱ ከዳነ ከጥቂት ሳምንት በኋላ በመሉ ሰውነት ላይ የሽፍታ ምልክት ይታያል። በእጅ እና በእግር መዳፍ ላይ ሽፍታ ይስተዋላል።  ሽፍታው የማሳከክ ስሜት የለውም እና በተጨማሪም አንዳንድ ሰዎች የፀጉር መርገፍ፣ የጡንቻ ህመም፣ ትኩሳት እና የጉሮሮ ህመም ያጋጥማቸዋል። እነዚህ ምልክቶች እየመጡና እየጠፉ ለዐመታት ሊቆዩ ይችላሉ።
  3. ሶሰተኛውና ደረጃ (TERITARY SYPHILIS) በጊዜ ህክምና ያላገኙ ታካሚዎች ሌሎች ተጓዳኝ የጤና እክሎች ያጋጥማቸዋል። ከነዚህም መካከል በአንጎል፣ በነርቮች፣ በዓይን፣ በልብ፣ በደም ሥሮች፣ በጉበት፣ በአጥንትና በመገጣጠሚያ ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

 

ክላሚዲያ (CHLAMYDIA)

ክላሚዲያ በባክቴሪያ የሚተላለፍ የአባላዘር በሽታ ሲሆን በቀላሉ የመዳን እድል አለው። እንደ ጨብጥ በሴቶች ላይ ምልክት አያሳይም። የክላሚዲያ ዋነኛ ምልክት በግንኙነት ጊዜ ያልተለመደ የሕመም ስሜት እና ከብልት ያልተለመደ ፈሳሽ ማየት ናቸው።  ክላሚዲያ በጊዜ ካልታከመ በሴቶች እና በወንዶች ላይ መሀንነትን ሊያስከትል ይችላል።

 

የአባላዘር በሽታዎች እና ተያያዥ ጉዳቶች

የአባላዘር በሽዎች ወዲያውኑ ከሚያስከትሉት ጉዳቶች የበለጠ ከባድ ችግሮችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ለምሳሌ፦

  •   የአባላዘር በሽታ ከእናት ወደ ልጅ ሲተላለፍ የፅንስ መጨንገፍ፣ የተወለዱ ህፃናት የክብደት መቀነስ፣ ወይም የህፃናት የአዕምሮ እድገት ውስንነት ሊያስከትል ይችላል።
  •   በተጨማሪም የኤችአይቪ ኤድስ ተጋላጭነትንም ይጨምራል

 

የአባላዘር በሽታዎች የመከላከያ መንገዶች

የአባላዘር በሽታዎችን በቀላሉ መከላከል ይቻላል። በተለይም የፆታ ግንኙነት የጀመረ ግለሰብ እራሱን እና አጋሩን እንዴት መጠበቅ እንደሚችል ማወቅ አለበት።

የአባላዘር በሽታዎችን ስርጭት ለመግታት በቀዳሚነት በፆታዊ ግንኙነት ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።

  •     በግንኙነት ጊዜ ኮንዶም መጠቀም
  •     የወሲብ አጋር አለማብዛት
  •     መታቀብ
  •     ምርመራዎችን እና ህክምናዎችን ማድረግ
  • በበሽታው የተያዘ ሰው በበሽታው ደግሞ ላለመያዝ እና  የአጋሩን ጤና ለመጠበቅ ለአጋሩ በሽታው እንዳለበት/እንዳለባት  በመግለፅ  አጋሩ ምልክት ባይኖራትም/ባይኖረውም ህክምና አንድታገኝ/እንዲያገኝ ማድረግ ተገቢ ነው።
  • የአባላዘር በሽታዎች ስርጭትን ለመቀነስ በቤት ውሰጥ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ከታዳጊ ልጆች ጋር ስለዚህ ጉዳይ በግልፅ ውይይት ማድረግ፣ በትምህርት ቤቶች የስነፆታ ትምህርት ማስፋፋትና ማጠናከር፣ የስነፆታ ጤና መረጃና ትምህርትን በተለይም በአባላዘር በሽታዎች የመተላለፊያ መንገዶች እና የመከላከያ መንገዶችን መረጃ ማቅረብ ይመከራል፡፡

 

የአባላዘር በሽታዎች ምርመራ

የአባላዘር በሽታዎች በአብዛኛው ጊዜ ምልክቶች አያሳዩም። ስለዚህ አብዛኛው በላብራቶሪ ምርመራ ላይ የተመሰረተ ነው። የደም የሽንት እና የፈሳሽ ምርመራ በሽታው መኖሩን እና አለመኖሩን ለማረጋገጥ ይጠቅማሉ።

ምርመራዎች የበሽታው መኖርና አለመኖሩን ከማረጋገጥ ባለፈም፦

  •   ምልክት የሚያሳዩትን ከማያሳዩት ለመለየት
  •   የፆታዊ ግንኙነት አጋር ተጋላጭነትን ለማረጋገጥ
  •   በእርግዝና ወቅት የፅንሱን ጤንነት ለማረጋገጥ
  •   ከተወለደም በኋላም የህፃኑን ጤንነት ለማረጋገጥ መጠቀም ይቻላል።

 

የአባላዘር በሽታዎች ሕክምና

  • አባላዘር በሽታ ህክምና በሚታዩት ምልክቶች ላይ ይወሰናል። እናም ህክምናውን ለመጀመር አብዛኛውን ጊዜ የላብራቶሪ ምርመራ አያስፈልግም። ሆኖም ግን አንዳንድ ግዜ እነዚህ ምርመራዎች አስፈላጊ ሆነው ከተገኙ በጤና ባለሙያዎች ታዘው ሊሰሩ ይችላሉ።
  • በአሁኑ ጊዜ ለበርካታ የአባላዘር በሽታዎች ዓይነት ውጤታማ የሆነ ሕክምና ማግኘት ይቻላል ክላሚዲያ፣ ቂጥኝ ጨብጥ እና አንድ ጥገኛ ተውሳክ የአባላዘር በሽታ አምጪ (ትሪኮሞኒያሲስ) በነጠላ በሚወስዱ መድሃኒቶች አማካኝነት በአብዛኛው ሊፈወሱ የሚችሉ ናቸው።
  • ለኸርፐስና (HERPES) ለኤች አይ (HIV) በጣም ውጤታማ የሆኑት መድኃኒቶች በሽታውን ሊፈውሱ ባይችሉም የበሽታውን አካሄድ ሊቀንሱ የሚችሉ ፀረ ቫይረስ መድኃኒቶች አሉ።

በሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፣ የአባላዘር በሽታዎች 9.4% እስከ 21% የሚሆን የስርጭት ስፋት አላቸው። ከዚህ ቁጥር ውስጥ አብዛኛውን ስፍራ የሚይዙት 15-24 እድሜ ክልል ወስጥ ያሉ ወጣቶች ናቸው በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በወጣቶች ዘንድ የአባላዘር በሽታ  ስርጭት እየጨመረ መጥቷል። በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኙ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የተካሄደ ጥናት የአባላዘር በሽታ ስርጭት 18.20% መሆኑን አረጋግጧል። ከበርካታ ሰዎች ጋር የጾታ ግንኙነት መፈፀም፣ በጾታ ግንኙነት ወቅት ኮንዶም አመጠቀም፣ እንዲሁም ወጣቶች ስለ አባላዘር በሽታ  ያላቸው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆን ለበሽታዉ መስፋፋት አስተዋፅኦ አድርጓል።

 

SOURCES

  •       World Health Organization. (n.d.). Sexually transmitted infections (stis). World Health Organization. https://www.who.int/health-topics/sexually-transmitted-infections#tab=tab_3
  •       Mayo Foundation for Medical Education and Research. (2023, September 8). Sexually transmitted diseases (stds). Mayo Clinic. https://www.mayoclinic.org/diseases-conditions/sexually-transmitted-diseases-stds/symptoms-causes/syc-20351240
  •       Elizabeth Boskey, P. (n.d.). The most common sexually transmitted infections (stis). Verywell Health. https://www.verywellhealth.com/the-most-common-stds-sexually-transmitted-diseases-3133040
  •       Kassie, B. A., Yenus, H., Berhe, R., & Kassahun, E. A. (2019, November 8). Prevalence of sexually transmitted infections and associated factors among the University of Gondar students, Northwest Ethiopia: A cross-sectional study – reproductive health. BioMed Central. https://reproductive-health-journal.biomedcentral.com/articles/10.1186/s12978-019-0815-5

 

የጤና ወግ 

ጠቃሚ እና የተረጋገጠ መረጃ ለጤናዎ ።

የጤና ወግን በነዚህ ሊንኮች መከታትል ይችላሉ ።

https://linktr.ee/Yetena_Weg

]]>
የወር አበባ ጊዜ ህመም (Dysmenorrhea) https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%8c%8a%e1%8b%9c-%e1%88%85%e1%88%98%e1%88%9d-dysmenorrhea/ Sat, 22 Jul 2023 19:36:41 +0000 https://yetenaweg.com/?p=3751 በረድኤት ወልደሩፋኤል(በቅ/ጳ/ሚ/ሜ/ኮ የ5ኛ አመት ተማሪ)  

By Rediet Wolderufael, C2 (5th year) medical student, SPHMMC

Approved by: Dr. Misikir Anberbir (Gynecologist/Obstetrician) 

 

የወር አበባ ጊዜ ህመም (Dysmenorrhea) ማለት ከየወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ህመም ሲሆን፤ በብዛት የሆድ ቁርጠት እና የወገብ  (የታችኛው ጀርባ) ህመም ስሜት አለው። በአንዳንዶች ላይ የታፋ ህመም ፣ ተቅማጥ፣ የማቅለሽለሽ ስሜት፣ ማስመለስ፣ ራስ ምታት እና ድካም ምልክቶች ሊኖሩት ይችላል።

የወር አበባ ከሚያዩ ሴቶች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በየወሩ ከ 1 እስከ 2 ቀን ድረስ ሕመም ያጋጥማቸዋል። አብዛኛውን ጊዜ ሕመሙ የለዘበ ነው። ይሁን እንጂ ለአንዳንድ ሴቶች ይህ ሕመም በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ በወር ውስጥ ለበርካታ ቀናት የተለመደውን እንቅስቃሴያቸውን እንዳያከናውኑ ይከለክላቸዋል።

ሁለት አይነት የወር አበባ ጊዜ ህመም አሉ። እነዚህም፦

  • ከበሽታ ጋር ያልተያያዘ የወር አበባ ጊዜ ህመም (Primary Dysmenorrhea) እና
  • ከበሽታ ጋር የተያያዘ የወር አበባ ጊዜ ህመም (Secondary Dysmenorrhea)

ከበሽታ ጋር ያልተያያዘ (Primary Dysmenorrhea) የሚከሰተው ፕሮስታግላንዲን በተባሉ ከማህፀን ግድግዳ ላይ ባሉ ተፈጥሯዊ ኬሚካሎች ምክንያት ነው። እነዚህ ኬሚካሎች (ፕሮስታግላንዲኖች) የማህፀን ጡንቻዎችና የደም ሥሮች እንዲኮማተሩ ያደርጋሉ። ‍ይህ መኮማተር ለህመሙ መንስኤ ይሆናል። የነዚህ ፕሮስታግላንዲኖች (ኬሚካሎች) መጠን የወር አበባ የመጀመሪያ ቀናት ላይ ከፍተኛ ስለሆነ ሕመሙም ከፍተኛ ነው። የደም መፍሰስ እየቀጠለና የወር አበባ እየፈሰሰ ሲሄድ የፕሮስታግላንዲኖች መጠን ይቀንሳል። ሕመምም ከመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት በኋላ የሚቀንሰው ለዚህ ነው። ይህ የወር አበባ ጊዜ ህመም የሚጀምረው አንዲት ልጅ የወር አበባ ማየት ከጀመረች ብዙም ሳይቆይ ነው። ብዙ ሴቶች ዕድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ የወር አበባ ጊዜ ህመም እየቀነሰ ይመጣል። ይህ ዓይነቱ ሕመም ከወሊድ በኋላም ሊሻሻል ይችላል።

ከበሽታ ጋር የተያያዘ (Secondary Dysmenorrhea) የሚከሰተው በመራቢያ አካላት ላይ በሚከሰት የጤና እክል ምክንያት ነው። ሕመሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሚሄድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ከተለመደው የወር አበባ ቁርጠት የበለጠ ጊዜ ይቆያል። በተጨማሪም ሕመሙ የሚጀምረው የወር አበባ ከመጀመሩ ከጥቂት ቀናት በፊት ሊሆን ይችላል። ሕመሙ እየተባባሰ ሊሄድና የወር አበባ መፍሰስ ካቆመ በኋላ ላይጠፋ ይችላል።

 

የወር አበባ ጊዜ ህመም እንዴት ማከም እንችላለን?

የወር አበባ ጊዜ ህመምን በርካታ የቤት ውስጥ ዘዴዎች ፣ የሕመም ማስታገሻ እና የሆርሞን ህክምና(hormonal therapy) በመጠቀም ማከም ይቻላል።

 

የቤት ውስጥ ዘዴዎች

  1. ሙቀት-በታችኛው ሆድ ላይ ማሞቂያ ፓድ ወይም ሙቅ ውሃ የያዘ ጠርሙስ በመጠቀም ማሞቅ ህመምን በእጅጉ ሊቀንስ ይችላል። የሕመም መቀነስ አቅሙም ከማስታገሻ መድሃኒት ጋር ተወዳዳሪ ሲሆን የማስታገሻ መድሃኒት እና ሙቀትን በጋራ መጠቀም የበለጠ ህመም የማጥፋት አቅም አለው። በጣም ሞቃት በሆነ የማሞቂያ ፓድ ወይም ትኩስ የውሃ ጠርሙስ ቆዳን ከማቃጠል መቆጠብ አስፈላጊ ነው፤ በግምት 40ºC (ለሰስ ያለ) ሙቀትን መጠቀም ይመከራል። ሙቀቱ አስፈላጊ ሆኖ በሚታሰብበት ጊዜ ሁሉ ልንጠቀመው እንችላለን።
  2. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ- በሳምንቱ ውስጥ አብዛኛውን ቀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ከማረግ ባለፈ ሕመምን የሚያግዱ ኬሚካሎችን ለማምረት ይረዳል። ለዚህም እንደ መራመድ፣ የሶምሶማ ሩጫ ፣ ሳይክል መንዳት ወይም መዋኘት የመሳሰሉት የኤሮቢክ እንቅስቃሴዎች ይመከራሉ።
  3. እንቅልፍ- ከወር አበባ በፊትና ወቅት በቂ እንቅልፍ መተኛት አስፈላጊ ነው። ጥሩ እረፍት ማግኘት የወር አበባ ጊዜ የሚያጋጥምን ህመም ለመቋቋም ሊረዳ ይችላል።

 

የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች

የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች (NSAIDs)-ህመምን እና ትኩሳትን የሚቀንሱ መድሃኒቶች ሲሆኑ፤ ከየወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሕመምን በመቀነስ ረገድ በጣም ውጤታማ የሆኑ መድኃኒቶች ናቸው። አንዳንድ የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች (NSAIDs) ያለ ሐኪም ማዘዣ መገኘት ይችላሉ፤ ከነዚህም አይቡፕሮፌን(Ibuprofen) በዋናነት ይጠቀሳል። እነዚህ መዳኒቶች (NSAIDs) የደም መፍሰስ ወይም ሌሎች የወር አበባ ምልክቶች እንደጀመሩ ወይም ከጀመሩ ከሁለት እስከ ሦስት ቀናት ባለ ጊዜ በቋሚ ፕሮግራም ከተወሰዱ በጣም ውጤታማ ናቸው ። የደም መፍሰስ ችግር፣ አስም፣ አስፕሪን አለርጂ፣ የጉበት ጉዳት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የአንጀት ቁስል፣ የጨጓራ ቁስል እና የመሳስሉት ተያያዥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች እነዚህን የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች (NSAIDsን) መውሰድ የለባቸውም። በተጨማሪም ስለ የወር አበባ ጊዜ ህመምን ማስታገሻ ጉዳይ ሃኪም ማማከር ይኖርባችዋል።

 

የሆርሞን ህክምና (hormonal therapy)  

  • የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች (ኪኒኖች) እና ሌሎች የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች (ለምሳሌ፡ መርፌ፣ ሉፕ (IUD) እና የቆዳ ስር የሚቀመጠው የወሊድ መከላከያ (ኢምፕላንት) የወር አበባ ጊዜ ህመም ላላቸው ሴቶች ውጤታማ ህክምናዎች ናቸው። እነዚህ መድሀኒቶች ፕሮስታግላንዲንን (ማህፀን እንዲኮማተር የሚያደርገው ኬሚካል) የሚያመርተው የማህፀን ግድግዳ በመቀነስ ሕመም፣ ቁርጠትና የወር አበባ መፍሰስ እንዲቀነስ ያደርጋሉ። ይህ ዘዴ በተለይ እርግዝናን መከላከል ለሚፈልጉ ሴቶች በጣም ጠቃሚ ነው ። ነገር ግን የወሲብ ግንኙነት የማያረጉ ሴቶችም ሊጠቀሙበት ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ ህክምናን ከሁለት እስከ ሶስት ወር ከተጠቀሙ በኋላ ከፍተኛ ለውጥ ይኖራቸዋል።
  • ሉፕ (IUD)- ሌቭኖርገስትሬል (ሚሬና) የተባለውን ሆርሞን የያዘው ሉፕ (IUD) ከላይ እንደተጠቀሱት የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች እና ሌሎች የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች የወር አበባ ጊዜ ህመምን 50 በመቶ ሊቀንስ ይችላል።

በተጠቀሱት ዘዴዎች ሕመሙ በበቂ ሁኔታ ካላስታገሰ ምን ማድረግ እንችላለን?

  1. ለየወር አበባ ጊዜ ህመም በጣም ውጤታማ የሆኑ ህክምናዎች የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች(NSAIDs) ፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ ኪኒኖች እና ሌሎች የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች ናቸው። ከእነዚህ የሕክምና ዓይነቶች አንዱ በሁለት ወይም በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ሕመሙን በበቂ ሁኔታ ካላስታገሰው ሌላ ሕክምና ሊሰጥ ይችላል። ለምሳሌ ያህል አንዲት ሴት የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች (NSAIDs) ሞክራ የወር አበባ ጊዜ ህመም ካልታገሰ፣ በሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች ምትክ ወይም በተጨማሪ የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ ልትወስድ ትችላለች።
  2. ከላይ የተጠቀሱት መንገዶች ሕመምን በሚገባ ካላሻሻሉ ቀጣዩ እርምጃ ከበሽታ ጋር የተያያዘ (Secondary Dysmenorrhea) ሊሆን ስለሚችል የወር አበባ ጊዜ ህመም መንስኤዎችን መመርመር እና ማከም ነው። ለዚህም ህክምና ቦታ በመሄድ ተገቢውን ምርመራ እና ህክምና ማግኘት ተገቢ ነው።

 

የጤና ወግ 

ጠቃሚ እና የተረጋገጠ መረጃ ለጤናዎ ።

የጤና ወግን በነዚህ ሊንኮች መከታትል ይችላሉ ።

https://linktr.ee/Yetena_Weg

]]>