2021 Article Writing Competition Winners – Yetenaweg and Engender Health https://srhr.yetenaweg.com Sexual and Reproductive health and rights (SRHR) in Ethiopia Sat, 24 Feb 2024 11:11:29 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.7 https://srhr.yetenaweg.com/wp-content/uploads/2024/01/yetenawegfinallogo-1-150x150.png 2021 Article Writing Competition Winners – Yetenaweg and Engender Health https://srhr.yetenaweg.com 32 32 የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ሳይከሰት ቀድሞ መከላከል ይቻላል ፡፡ https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%88%85%e1%8d%80%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%8c%ab%e1%8d%8d-%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad-%e1%88%b3%e1%8b%ad%e1%8a%a8%e1%88%b0%e1%89%b5-%e1%89%80%e1%8b%b5%e1%88%9e/ Mon, 05 Sep 2022 03:48:40 +0000 https://yetenaweg.com/?p=2917 የማህፀን በር ጫፍ ካንሰርየቅድመ ካንሰር ምርመራ

(ህዋሶች ) ከተለመደው ወጣ ባለ እና ጤናማ ባልሆነ መልኩ ሲያድጉ እና ሲባዙ ይፈጠራል ።

 የማህጸን በር ካንሰር በማህጸን አካባቢ ያሉ የሰውነት ክፍሎችን ሊወር፣ ወደሌላ የሰውነት ክፍሎቻችንም ሊሰራጭ ይችላል

በአለማችን ያሉ ሴቶችን በብዛት ከሚያጠቁ የካንሰር በሽታዎች አራተኛውን ደረጃ የያዘው የማህፀን ጫፍ

ካንሰር የሚባለው የካንሰር ዓይነት ነው፡፡ ይህን በሽታ ለየት የሚያደርገው 80% በላይ የሚያጠቃዉ መካከለኛና

ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች የሚኖሩ ሴቶችን መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ቅድሚያ በሚሰጡ ክትባቶች እንዲሁም በግዜ

አግኝቶ ለማከም የሚረዳውን (papsmear) የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ በማድረግ መከላከል ይቻላል፡፡

 

  • አጋላጭ መንገዶች

የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ዋናዎቹ አጋላጭ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

  1. (HPV) ቫይረስ

ሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ  በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፍ ቫይረስ ሲሆን  የማህጸን በር ካንሰር ዋናው አጋላጭ ነው። ከ99% በላይ የሚሆነው የማህፀን በር ካንሰር ከዚህ ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነው። ምንጭ :WHO

ይህ ቫይረስ ብዙውን ጊዜ በሽታው ምልክቶች ሳይኖሩት በሰውነት ውስጥ ኖሮ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ሊያመጣ ይችላል፡፡

ይህን ለመከላከል የሚረዳ ክትባት እድሚያቸው 17 – 25 እንዲሁም 25-40 ዓመት ላሉ ሴቶች መስጠት ተጀምሯል፡፡

. ሲጋራማጨስ

. የአባላዘር በሽታ የተያዙ ሴቶች (HIV) ጨምሮ

. ለረጅም ጊዜ ማለትም 5 አመት በላይ በክኒን የሚወሰዱ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል የሚወስዱ

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ መንገዶች በጥቂቱ ምክንያት ሊሆኑ ቢችሉም በተለይ HPV ቫይረስ መጠቃት ግን በሁሉም

በበለጠ ተፅእኖ የሚያመጣ መንገድ ነዉ፡፡

 

  ምልክቶች

      የማህፀን ጫፍ ካንሰር ወደ ውስጠኛው የማህፀን በር ክፍል ገብቶ በደንብ ከመዛመቱ በፊት በተያዘችው ሴት ላይ ምንም ዓይነት ምልክቶች አያሳይም፡፡

  ይህም ነው የማህፀን ጫፍ ምርመራ (papsmear) ለሁሉም 22 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ቢያንስ በዓመት አንዴ መመርመር በጣም አስፈላጊ እንደሆነ የሚነገረዉ፡፡

  ከመዛመቱ በፊት ማወቅ ከተቻለ ከነጭራሹ ማጥፋት ይችላል፡፡  ይህ ሊሆን ካልቻለ ግን ምልክቶቹ

. ከወር አበባውጪከማህፀንየደምመፍሰስ

. በግንኙነት ጊዜ ህመም ወይም መድማት መኖር

. ሀይለኛ ሽታ ያለው የማህፀን ፈሳሽ መኖር

. እንዲሁም የማህፀን አካባቢ ህመም እንደ ምልክት ሊታይ ይችላል፡፡

ህክምና

       አንዲት ሴት የማህፀን ካንሰር መያዟ ከታወቀ በኋላ በመጀመሪያ የተዛመተበት ደረጃ መታወቅ አለበት፡፡  ይህንን በመመርኮዝ ህክምናውን መምረጥና መስጠት ይቻላል፡፡

 ደረጃውም የሚወስነው ከማህፀን ጫፍ ላይ  ብቻ መሆኑን ወይም ከዛ አልፎ የሰውነት  ማጣሪያ ዕጢዎች (lymphnodes) መግባቱን እንዲሁም ከዛም

  አልፎ ወደ ሌሎች የሰዉኑት ክፍሎች መዛመቱን በማረጋገጥ ነው፡፡ 

 እነዚህ ህክምናዎች የሚከተሉት ናቸው

  በማህፀን ጫፍ ላይ የተወሰነ ከሆነ በቀዝቃዛ ናይትሮጅን አማካኝነት የካንሰሩን ቦታ የማጥፋት ህክምና (cryotherapy). ከዚህ አልፎ ወደ ሁለተኛው ክፍል ከገባ የጨረር  እንዲሁም

የኬሞቴራፒ ህክምና ከማህፀን ጫፍ ቀዶ ጥገና ጋር  በመጨረሻም ወደሌሎች የሰውነት ክፍሎች ከተዛመተ ሙሉ የማህፀን ማውጣት ቀዶ ጥገናን ጨምሮ የጨረርና

 የኬሞቴራፒ ህክምና ሊያሳፈልግ ይችላል፡፡

ይህ ካንሰር ሳይከሰት ቀድሞ መከላከል ይቻላልን?

. የሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ ክትባት በወቅቱ በመውሰድ

. የ HPV ቫይረስ ክትባት በመውሰድ ይህንን 270,000 በላይ ሴቶች በአመት የሚገድለውን አደገኛ ካንሰር መካላከል ትችላለች፡፡

. የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ሁሉም ሴቶች አስራ አምስት አመት ሳይሞላቸው ክትባቱን እንዲውስዱ ይመክራል።

. የሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ ክትባት የማህጸን በር ካንሰር አምጪ ከሆኑት የሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረሶች  ይከላከላል

 

  •  የቅድመ ካንሰር ምርመራ 

ማንኛዋም ሴት እድሜዋ 21 አመት ከሆነበት ወይም ግንኙነት ከጀመረችበት ከ3 አመት ጀምሮ በየ3  አመቱ ፓፕ ስሚር የተሰኘውን ምርመራ ብታደርግ።

ፓፕ ስሚር በማህጸን በር ላይ ጤናማ ያልሆኑ ቅድመ ካንሰር ለውጦች ካሉ ለመፈተሽ በጤና ባለሞያዎች የሚደረግ ምርመራ ነው። ጤናማ ያልሆኑ ለውጦች ከታዩ ክትትል እና አስፈላጊው ህክምና ይደረጋል ።

]]>
ቅድመ ወሊድ እና በ እርግዝና ጊዜ የ ሚያስፈልገን ክትትል። https://srhr.yetenaweg.com/%e1%89%85%e1%8b%b5%e1%88%98-%e1%8b%88%e1%88%8a%e1%8b%b5-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%89%a0-%e1%8a%a5%e1%88%ad%e1%8c%8d%e1%8b%9d%e1%8a%93-%e1%8c%8a%e1%8b%9c-%e1%8b%a8-%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%8d%88/ Mon, 05 Sep 2022 03:43:04 +0000 https://yetenaweg.com/?p=2914 በእርግዝና ጊዜ የተለመዱ የህመም ምልክቶች

  • በእርግዝና ጊዜ የተለመዱ የህመም ምልክቶቸ የቶቹ ናቸው ?

         ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የተለያዩ ለውጦች በሰውነት ላይ ይከሰታሉ፡፡ ይህም የሚሆነው የሰውነት ሆርሞኖችና የስራ ሂደቶች ስለሚጨመሩ ነው፡፡

  በሰውነት ላይ የሚፈጠረው ጫና አንዳንድ የህመም ምልክቶች ሊያመጣ ሲችል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዋናዎች ናቸው፡፡

የድድ መድማት

        ድዳችን በእርግዝና ጊዜ ለስላሳ ሲሆን ሊያብጥና ቆሻሻ የማጥራት አቅሙ ሊደክም ይችላል ይህም የሚሆነው በሆርምኖች መጨመር ሲሆን ይህ ሲያጋጥም የድድ

   መድማትና  መጠዝጠዝ ሊኖር  ይችላል፡፡ ይህንንም ለመከላከል በደንብ ጥርስን ማፅዳትና ለጥርስ ማጠንከሪያ የሚመከሩ  ምግቦች መመገብ ያስፈልጋል፡፡

ትንፋሽ መቆራረጥና የማዞር ስሜት

     የሳንባችንን ክፍል ከሆድ እቃችን የሚለየው  ዳያፍራም የተባለው ጡንቻ በእርግዝናው ጫና ምክንያት ወደላይ ሊገፋ ስለሚችል ትንፋሽ መቆራረጥ ያመጣል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የደም ማነሰ ወይም የደምግፊት መቀነስ የማዞር ስሜት ሊያመጣ ይችላል ይህ ሲሆን ቀና ብሎ በመተኛት ማዞር ሲኖር ደግሞ ቁጭ ባሉበት

ጭንቅላትን እግር መሀል በመቅበር እና ባጠቃላይ እረፍት በማድረግ መከላከል ይቻላል፡፡

በየጊዜው የሽንት ማስቸገርና የሽንት ማምለጥ

     ማህፀን ውስጥ የሚያድገው ህፃን የሽንት ከረጢት ላይ ጫና ስለሚፈጥር በተደጋጋሚ ሽንት መምጣትና በተለይ በመሳቅና በማስነጠስ ጊዜ ሽንት

ሊያመልጥ ይችላል፡፡ ይህ ብዙም ሊያሳስብ አይገባም፡፡ ከሰዓት ይምትጠጣውን የውሃ መጠን በትንሹ በመቀነስ መከለከል ይቻላል፡፡

የማህፀንና የሰውነት አካባቢ ማሳከክና ሸንተረር ምልክቶች መውጣት

     የሚያልቡ የሰውነት ክፍሎች አካባቢ ለምሳሌ አንገት ስር የሰውነት መገጣጠሚያ እንዲሁም የማህፀን በር ጋር መድረቅ ማሳከክና ማቃጠል ሊኖር ይችላል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ቆዳችን ሲወጠር ነጭ እና ጥቋቁር የሽንተረር ምልክቶች በተለምዶ እግርና ሆድ ላይ ይታያሉ፡፡ ይህ ተፈጥሮአዊ ለውጥ ስለሆነ ማሰብ አይገባም

የሆድ ድርቀትና የፋንጢጣ አካባቢ እብጠት (Hemorrhoid)

በእርግዝና ጊዜ የሚመረቱ ሆርሞኖች የምግብ አፈጫጨት ፍጥነትን ስለሚቀንሱ የሆድ ድርቀትን ያመጣሉ፡፡ ይህ ሆዳችን ላይ እርግዝናው ከሚያመጣው ጫና ጋር ተያይዞ

 የፊንጢጣ አካባቢ እብጠት (ኪንታሮት) ሊያመጣ ይችላል፡፡

    ይህ እንዳይከሰት የሆድ ድርቀትን የሚከላከል ምግቦች እንደ ጎመን ዝንጅብል የካስተር ዘይት የመሳሰሉትን ምግቦች በመዉሰድ መቀነስ ይቻላል፡፡

ቁርጥማትና የደምስሮች ማበጥና መወጣጠር (varicose veins)

      በእርግዝና ጊዜ የመገጣጠሚያ የእግር እንዲሁም የእጅ ጫፎች ቁርጥማት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህ ችግር ከካልስየም ወይም ቫይታሚን እጥረት ሊሆን

 ስለሚችል እንደ ወተት ነጭ ሽንኩርት ወይም በየትኛውም የመድሀኒት መደብር የሚሸጡ የቫይታሚን እንክብሎች መውሰድ ይመከራል፡፡ ሌላው  ደግሞ

 የሚቆረጥመው  ቦታ በጣት ከፍ አድርጎ ከስር ማሸት ግዜያዊ ዕረፍት ያስገኛል፡፡ የደም ስሮች ማበጥ ሲኖር ደግሞ እግርን ከፍ አርጎ በመቀመጥ እንዲሁም

 ለዚሁ ብለው የተዘጋጁ ማሰሪያዎችን ከመድሀኒት ቤት በመግዛት ማድረግ ዕረፍት ያስገኛል፡፡

 

የጨጓራ ማቃጠል (ቃር), የማቅለሽለሽና ትውከት ህመም

      የምግብ ቱቦን ከጨጓራ የሚለየው ማሰርያ በሆርምን ለውጦች ስለሚለሰልስ የጨጓራ አሲድ ወደ ምግብ ቱቦ ሲመለስ  ቃር ያመጣል፡፡ ይህን ለመቀነስ

 ከባድና ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች መቀነስ ይመከራል፡፡ ካሞሜላ ሻይ ዝንጅብል እና ንፁህ የተፈላ ወተት መጠጣት  ለጨጓራ ጥሩ ነው፡፡

በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ወራት በተለይ ምግብ ሲሸትና ጠዋት ጠዋት ማቅለሽለሽ እንዲሁም ማስታወክ ሊኖር ይችላል፡፡ ይህ ችግር ሲያጋጥም

የሚያስጠላትንና ከባድ ምግቦችን; በማቆም ደረቅ ብስኩቶችን, በዝንጅብልና በካሞሜላ የተሰሩ ሻዮችን መውሰድ አነስ ያሉ ምግቦችን በየሁለት ሰዓቱ መመገብ ከባሰም  የጤና ባለሙያ ማማከር  ያስፈልጋል፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች በጣም በተደጋጋሚ ሊታዩ ስለሚችሉ ብዙ ሊያስጨንቆት አይገባም፡፡  

እርግዝና ሲከሰት የሚደረጉ ጥንቃቄዎች

ማጨስ መተው

     ማጨስ ለተረገዘው ህፃን የኦክስጅን እጥረት ያመጣል፡፡ ከዚህም ባሻገር ውርጃን ያለጊዜ የፅንስ መውረድንና ክብደታቸው ትንሽ የሆኑ ህፃናት

እንዲወለዱ ያደርጋልአፈጣጠራቸው ችግር ያለበት ህፃናትም እንዲወለዱ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ሲጋራ ካናቢስ እና ሺሻ ያሉ በመጨስ የሚወሰዱ

እፆችን ከናካቴው መተው ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ከቤተሰቡ ወይም ካካባቢዉ የሚያጨስ ሰው ካለ እነዚህ ኬሚካሎች አየሩ ውስጥ ስለሚገኙ

ይሄንም ከተሳቢነት ማስገባት ያስፈልጋል፡፡

አልኮል መተው

       ለአንዲት እርጉዝ ሴት በቀን ከአንድ ብርጭቆ ወይን በላይ አልኮል አይመከርም; አልኮል በብዛት ከመዉሰድ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ይህፃናት

የአእምሮ አፈጣጠር ችግርና በሽታ አለ ስለዚህ ይህን ለመከላከል የአልኮል መጠኗን መቀነስ ከተቻለም ማቆም ያሻል፡፡

 

መድሀኒቶች

        ለሌላ ጊዜ በቀላሉ ምንም ችግር የማይኖራቸው እንደ አስፕሪን ያሉ መድሀኒቶች ለእርጉዝ ሴቶች የተለወጠ የሰውነት የሆርሞኖች መጠን ሊጎዱ

ስለሚችሉ ማንኛውም መድሀኒት ለዶ/ ሳያማክሩ መወሰድ የለበትም፡፡ የማይቋረጡ መድሀኒቶች አንደ ደም ግፊት ስኳር እና HIV ያሉ ህመሞች

ያለባቸው እርጉዝ እናቶች በተለየ የክትትል ሂደት መድሀኒታቸው / ባዘዘው መሠረት መወሰድ አለበት፡፡

ሌሎች

        ጥሬ ነገሮች ባለመመገብ በተለይ ስጋ እንዲሁም በቤት ውስጥ ድመቶች ወይም ውሾች የሚፀዳዱበትን አፈር በተገቢው መንገድና በንፅህና

በማስወገድ በእርግዝና ጊዜ ጐጂ የሆነ (toxoplasmosis) የተባለውን ተህዋስያን መከላከል ይቻላል፡፡

 

የተለየ ክትትል የሚፈልጉ የዕርግዝና አይነቶች

     ብዙ የዕርግዝና ክትትሎች ከዚህ ቀደም ከተጠቀሱ የክትትል ሂደቶች ዉጪ የተለየ ምርመራ  ባያስፈልጋቸውም አንዳንድ ለየት ያለ ወይም በብዛት ቀጠሮ

እንዲሁም ምርመራ የሚያስፈልጋቸው የዕርግዝና ዓይነቶች አሉ፡፡ ይህም ለህፃናኑ እንዲሁም ለእናት አስጊ የሆኑ ችግሮችን ቀደሞ ለመከላከል ይረዳል

 

የደም ማነስ

      ብዙ እናቶች ከእርግዝና በፊት የደም ማነስ ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ ይህ የደም ማነስ በቅድሚያ መስተካከል ይኖርበታል የእናቲቱን እና የህፃኑን እድገት ለማጎልበት

እንዲሁም በምጥ ጊዜ በሚመጣ መድማት ጉዳትን ለመከላከል በብረት የበለፀጉ ምግቦችን እንዲሁም በዶክተር የሚታዘዙ የብረት እንክብሎችን መውሰድ ያስፈልጋል፡፡

እነዚህ የምግብ አይነቶች ቀይ ስጋ.ቆስጣ አሳ ዶሮ እና ኮክ የመሳሰሉ ምግቦችን ያጠቃልላል፡፡

 

ስኳር በሽታ

      ከማርገዝ በፊትም ሆነ በእርግዝና ወቅት ብቻ የሚወጣ የስኳር በሽታ ተቆጣጥሮ መያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም የሚሆነው በየጊዜው የስኳር መጠንና ተያያዥ ምርመራ

በማድረግ, የመድሀኒት አጠቃቀምን በማስተካከልና መድሀኒቱ ስኳሩን መቆጣጠሩን በማረጋገጥ ነው፡፡ ኢንሱሊን የሚወስዱ እርጉዝ ሴቶች የሚወስዱት መጠን በዶ/

መስተካከል አለበት ምክንያቱም እርግዝና የሰውነት እንዲሁም የውስጣዊ የሰውነት አሰራርን ሊቀይር ስለሚችል ነው፡፡ከዚህ  ጋር ተያይዞ አመጋገብን እና የሰውነት ክብደትን መከታተልም ተመራጭ ነው፡፡

 

የማህፀን በር መሳሳት

          በጤናማ የእርግዝና ወቅት የማህፀን በር ምጥ እስኪመጣ ድረስ ተዘግቶ ይቆያል፡፡አንዳንድ እናቶች ግን ጊዜው ሳይደርስ በተለያዩ የጤና መታወኮች  ምክንያት

ተደጋጋሚ ውርጃ ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ ይህን ለመከላከል ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይመከራል፡፡

 

 የደም ግፊት

       ከእርግዝና በፊትም ሆነ በእርግዝና ጊዜ ብቻ የሚወጣ የደም ግፊት በሽታ የተለየ የእርግዝና ክትትል ያስፈልገዋል፡፡ በእርግዝና የመጀመሪያው ጥቂት ወራት የደም

ግፊት መጨመር በፈጥነት ክብደት መጨመር የእግር ማበጥ ራስ ምታት የዓይን ብዥታ የሆድ ቁርጠት ሲኖር የደም ግፊት በሽታ ምልክቶች  ሊታይ ስለሚችል ወደ

ሆስፒታል መምጣትና ክትትል ማደረግ ያስፈልጋል፡፡

    የግፊት በሽታ ያለመድሀኒት ወይም ክትትል በጣም ከፍ ካለ ለህፃኑ የአፈጣጠር እና አድገት ችግር እንዲሁም ለእናት ከፍተኛ የጉበት እንዲሁም የኩላሊት መጎዳት

ሊያመጣ ይችላል ፡፡ ከዚህም አልፎ ራስን እስከመሳት ሊያደርስ ይችላል፡፡ እነዚህ ችግሮች እንዳይከስቱ የሚሰጡ መድሀኒቶችን እና ምክሮችን ማግኘት ያስፈልጋል

                                                                       

  Rh-ve (ሾተላይ) የደም ዓይነት ልዩነት

      ከአለማችን ሴቶች ወደ 15-20% ያሉት የደም አይነታቸው Rh-ve ሲሆን በመጀመሪያ ሳይሆን በሁለተኛው እርግዝናና ዉልደት ጊዜ ቀድመው የወለዱት ልጅ

 የተለየ የደምአይነት (Rh+ve) ከሆነ ለሚመጣው ሁለተኛ እርግዝና ችግር ሊፊጥር ስለሚችል የተለየ ክትትል መጀመር ያሻል፡፡ ይህን ችግር የሚከላከሉ መድሀኒቶች

ለማግኘትም ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል፡፡

 

 ለእርግዝና ወራቸው በመጠን ያነሱ ወይም የበለጡ ህፃናት

     ለአያንዳንዱ የእርግዝና ወራት ተስተካካይ የሆነ የህፃን የመጠን መለኪያ  ስሌት ሲኖር  ከዚህ በላይ ወይም በታች ሲሆን አንዲት እርጉዝ ሴት የተለየ ክትትል መጀመር

አለባት፡፡ይህ የሚሆነዉ በተለያየ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል የህፃኑን  ህልውና  እንዲሁም የእናቴቱን ጤንነት ለመጠበቅ ቅርብ ክትትል ያስፈልጋል፡፡

 

 መንታ እርግዝና

    ከማንኛውም እርግዝና በተለየ መልኩ የመንታ ወይም ከአንደ በላይ ህፃናት  በአንዴ እርግዝና በሰውነት ላይም ሆነ በህፃናቱ አቅምና አስተዳደግ ላይ

የተለየ ጫና ያሳድራል፡፡እነዚህን ጫናዎች ቀድሞ ለመከላከል እንዲሁም ከመጡም ለመቀነስ የተለየ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ለምሳሌ አንደ የደምግፊት መጨመር,

የሽንት ውሀ ቀድሞ መፍሰስበእርግዝና ወቅት የሚመጣ መድማት, የደም ማነስና ያለጊዜ የሚመጣ ምጥ ከማንኛውም እርግዝና በበለጠ የመንታ እርግዝናን የማጥቃት

መጠኑ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ስለአመጋገብስለሚደረጉ ጥንቃቄዎች እና ተያያዥ ጉዳዮች / ጋር መማከር ያስፈልጋል፡፡

 

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የማህፀን ደም መፍሰስ

 

       በእርግዝና ጊዜ ማንኛውም የማህፀን የደም መፍሰስ ሲከሰት በፍጥነት የጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል፡፡ 28 ሳምንት በፍት የውርጃ ምልክቶች ሊሆኑ

 ስለሚችሉ ከዛም በኋላበእንግዴ ልጁም ሆነ በሌላ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል የጤና ተቋም መሄድና /ርዎትን ማናገር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ብዙ የደም መፍሰስ

 ካጋጠመ ደም መውሰድ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ከዚህም ጋር በተያያዘ የህፃኑንና የእርግዝናውን ሁኔታ መከታተል ጠቃሚ ስለሆነ ነው፡፡

  ከእነዚህ ህክምናዎች በኋላ መድማት ካላቆመ ደግሞ በጥንቃቄ ጤናማ የሆነ የማዋለድ አገልግሎት ለማግኘትም ወደ ጤና ተቋም መሄድ አስፈላጊ ነው፡፡

 

በእርግዝና ጊዜ ሊታዩ የሚችሉ አደገኛ ምልክቶች

1. ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት እና የሆድ ቁርጠት ከእምብርት በታች

2. ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት እና የአይን ብዥታ

3. የእጅና የፊት እብጠት

4. በማህጸን ደም መፍሰስ

5. የጽንስ እንቅስቃሴ መቀነስ ወይም መቆም

6. የሽርት ውሀ ከምጥ በፊት መፍሰስ

*እንዚህ ምልክቶች በማንኛውም ጊዜ ከታዩ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል

 

 

 

 

 

 

]]>
የጨቅላ ህፃናት እንከብካቤና ጥንቃቄ ለወላጆች https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%8c%a8%e1%89%85%e1%88%8b-%e1%88%85%e1%8d%83%e1%8a%93%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8a%a8%e1%89%a5%e1%8a%ab%e1%89%a4%e1%8a%93-%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%83%e1%89%84-%e1%88%88%e1%8b%88/ Mon, 05 Sep 2022 03:33:22 +0000 https://yetenaweg.com/?p=2910 በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ እናትና አባት የሆኑ ወላጆች ጨቅላ ህፃናት ወደ ቤታቸው ይዘው

ከሄዱ በኋላ እንዴት መንከባከብ እንደለባቸውና ድንገተኛና አሳሳቢ የሆኑ ምልክቶች የቶቹ እንደሆኑ

ለማወቅ አዳጋች ሊሆን ይችላል፡፡ የሚከተሉት ነጥቦች እንዴት መንከባከብ እንደሚቻልና ምን ምን

ምልክቶች  ማየት እንደሚገባ ለማወቅ ይረዳል፡፡

በእንቅልፍ ጊዜ

       ጨቅላ ህፃናት እናታቸው ማህፀን ውስጥ ሳሉ የለመዱትን ድምፅ፣ ሙቀት፣ እንቅስቃሴ እንዲሁም

ብርሃን ካገኙ በሰላም ለመተኛት እና ከነቁም በረጋ ሁኔታ እንዲቆዩ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ስለዚህ

ጥሩ ሙቀት እንዲሰማቸው ነገር ግን ላብ እንዳያስችራቸው በመጀመሪያ በንፁህ ደረቅ ካኒቴራ፣ ሱሪ

ካልሲና ኮፍያ አልብሶ ከዚያም በህፃን ብርድልብስ አየር እንዳይገባ አድርጎ በመጠቅለል ሙቀት  መስጠት

ይችላል፡፡ ያሉበት ክፍል ፀጥ ያለ ንፁህ አየር የሚገባበት ብርሃኑ ለአይናቸው እንዳይከብድ ዝቅ ያለ ሲሆን

በሰላም እንቅልፍ ያገኛሉ፡፡

 

 በመመገብ ጊዜ

         ጨቅላ ህፃናት በየ 2-3 ሰዓት ውስጥ እስከ 60 ሚሊ ሊትር የጡትም ሆነ የዱቄት ወተት

ያስፈልጋቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ እንደ ጣት መምጠት፣ አፍ መክፈት ወይም ማልቀስ ምልክት ቢያሳዩም

ተኝተው እንኳን  ቢሆን እየቀሰቀሱ ማጥባት ተገቢ ነው፡፡ ከጠቡም በኋላ ከአንገት ቀና  አድርጎ ደረት

ላይ በመለጠፍ  ወይም በመያዝ ድምፅ አውጥተው እንኪያገሱ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡

 

በፅዳት ጊዜ

 

       ጨቅላ ህፃናት እትብታቸው ደርቆ እስኪወድቅ ድረስ በዋይፐር ወይም በርጥብ ጨርቅ ብቻ

መጠረግ አለባቸው፡፡ ከዚያም በኋላ ለብ ባለ ውሃ ለህፃናት በተመረጡ ለስላሳ ሳሙናዎች በጥንቃቄ

ማጠብ ተገቢ ነው፡፡ የሽንት ጨርቃቸው በየጊዜው እንዳይቆሽሽ በመቀየር ሲቀየርም ቆሻሻው

ሰውነታቸውን እንዳይጎዳ በመጠራረግ ፓውደር በመቀባት መንከባከብ ይመከራል፡፡

 

የማያሳስቡ ምልክቶች

       ጨቅላ ህፃናት በመጀመሪያው ወር አመጋገብ አተነፋፈስ እና እንቅስቃሴ አዲስ ስለሆኑ በተደጋጋሚ

ማቀርሸት/ወደላይ ማለት፣ መጥባት ማስቸገር፣ ቶሎ አለማግሳ፣ ሲተነፍሱ ሲርሲር የሚል ድምፅ መስማት፣

ጭንቅ ያለ አተነፋፈስ፣ አፍንጫ መታፈን፣ በደምብ አለመተኛት እና በተደጋጋሚ ማልቀስ የመሳሰሉት

ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ምልክቶች በጊዜ ስለሚጠፋ ወላጆች ታግሰው በተረጋጋ መንፈስ ማሳለፍ

ደገባቸዋል፡፡

 

ድንገተኛ የሆኑ አሳሳቢ ምልክቶች

 

ወላጆች ቀጥሎ የተዘረዘሩት ምልክቶች ጨቅላ ልጆቻቸው ላይ ሲታይ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም ማምጣት

ይኖርባቸዋል፡፡

    • . መጥባት

ማቆምወይምበተደጋጋሚማስመለስናማስቀመጥ

. የፊትና ሰውነት ቢጫ መሆን

. የሆድ ማበጥና ሰገራ ማስወጣት ማቆም

ማንቀጥቀጥ

. የከንፈርና የእግር እጅ ጫፎች ሰማያዊ ወይም ጥቁር ቀለም መያዝ

. ያለማቋረጥ ማቃሰት በጣም መደካከም

. በፍጥነትና ደረታቸው ወደውስጥ እስኪገባ መተንፈስ

. ትኩሳት

. የእትብት ማበጥ መቅላት ወይም ሳያቋርጥ መድማት

. የዓይን ቅላትና ቢጫ ፍሳሽ መውጣት፡፡

ለህፃናት ስለሚሰጡ ክትባቶች 

አንድ ህፃን አንድየተወለደ/  በየጊዜው  መወሰድ ያለበት  ክትባቶች ወላጆች አሰታውሰው ማስከተብ አለባቸው፡፡

ክትባት ማለት ለአንድ ለሚተላለፍ በሽታ መከላከያ አስቀድሞ የሚወሰድ መድሀኒት ሲሆን የሰውን የራሱን የመከላከል 

 አቅም በማዳበርና የመከላከያ ኬሚካሎች እንዲያመርት በማድረግ በሽታን ከመምጣቱ በፊት ይከላከላል፡፡                   

 ክትባቶች በአመት 2-3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በበሽታ እንዳይያዙ ሲከላከል በበሽታው የተያዙ ሰዎች በአካባቢው   ቢኖሩ እንኳን ወደ ሰውነት ዘልቆ ገብቶ በሽታ እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡

 

የክትባት አሰጣጥ

ክትባቶች ብዙዎቹ በመርፌ መልክ በቆዳ የሚሰጡ  ሲሆኑ አንዳንዶቹ  በአፍ ጠብታ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡

 

ክትባት የሚከላከላቸው 7 የህፃናት በሽታዎች 

 

ዲፕቴሪያ(Diptheria)

ይህ በሽታ ወፍራም ፈሳሽ ጉሮሮ ውስጥ በማከማቸትና ሳንባን በማፈንና እንዲሁም ለመተንፈስ በመከልከል                             

የሚያጠቃ ካለታከሙ ለሞት የሚዳርግ በሽታ ነው፡፡

Tetanus (መንጋጋ ቆልፍ)

የሰውነትን ጡንቻ በተለይ የመንጋጋ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎችን በማጠንከር መተንፈስ እነዲከብዳቸው ያደርጋል፡፡           

በመንጋጋ ቆልፍ ከሚያዙ 10 ህፃናት አንዱበሞት ይቀጠፋል፡፡

 

Pertusis (ትክትክ)

በጣም ከባድ የሆነ የማያቋርጥ ሀይለኛ ሳል ማስመለስ መተንፈስ  እስኪከብድ ድረስ ሲኖር ትክትክ በሽታ ህፃኑ ሊኖርበት         

  ይችላል፡፡

Measles (ኩፍኝ) /mumps(ጆሮ ደግፍ)MMR

ኩፍኝና  ጆሮ ደግፍ በቫይረስ የሚመጡ በሽታዎች ሲሆኑ የሰውነት ላይሽፍታዎችና ማሳከክ ሊኖር ይችላል፡፡ አንገት ስር           

 በግራና በቀኝ ከትኩሳትና ከህመም ጋር የተያያዘ እብጠት ሲኖር ደግሞ የጆሮ ደግፍ ምልክቶች

ናቸው እነዚህ በሽታዎች ብዙ ጊዜ ለህይወት የሚያሰጉ በሽታዎች ባይሆኑም ህፃናቶችን

እንዲሁም ትንንሽ ልጆችን ያሰቃያሉ፡፡

የህፃናት የሳንባ ምች (pnemocucus ,H.lnfluenza)Hib

አንድህፃን በተለይ 5 አመት በታች  ሆኖ ራስምታት ሳልና የአተነፋፈስ ችግር ካለበት የሳንባምች በሽታ የተያዘ ሊሆን ይችላል               

 ይህንን አደገኛ በሽታ ለመከላከል የሚጠቅሙክትባቶችን ገና በልጅነቱ ካገኘ ግን ከነዚህ በሽታዎች ይጠበቃል፡፡

ሄቨታይተስ (hepatitis B)

የአይን ወይም የሰውነት ቢጫ መሆንና ተቅማጥ ማስመለስ መደካከም የጡንቻዎች የመገጣጠሚያ ወይም ሆድ ህመም የሄቨታይተስ               

በሽታ በህፃናት ሲከሰቱ ከምናያቸው ምልክቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ፖሊዮ (polio) OPV

ይህ በሽታ በተለይ እንደኛ አይነት ሶስተኛ አለም አገራት የእግር አፈጣጠር ችግር ከሚያመጡ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በክትባት

መከላከል የሚቻል ክምድረገፅ ሊጠፋ የተቃረበ በሽታ ነው፡፡

 

የክትባት አሰጣጥ ጊዜ ፕሮግራም

 የክትባት የጎንዮሽ ምልክቶች

አንድ ህፃን ክትባት ሲከተብ ከበሽታው ከራሱ የተሰራ መከላከያ በመሆኑ የጎንዮሽ አንዳንድ የማያሳስቡ ምልክቶች ሊኖሩ                 

 ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ

    • . መጠነኛ

ትኩሳት

. የተከተበበት ቦታ ማበጥ ሲነካ ማመም ቀይመሆን

. መደካከም የምግብ ፍላጎት መቀነስ

. ማስመለስ

ምናልባት የሚያሳስቡና በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም ሊያመጡ የሚገባቸው ምልክቶች

    • . ማዞር

እጅግመደካከም

. ማንቀጥቀጥ

. ሰውነት ላይ ሽፍታ መውጣት

. የፊት ጉሮሮ ጋር ማበጥ መተንፈስ መክበድ

 

 

 

 

 

]]>
አመታዊ የጤና ምርመራ https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%89%b3%e1%8b%8a-%e1%8b%a8%e1%8c%a4%e1%8a%93-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%88%98%e1%88%ab/ Mon, 05 Sep 2022 03:22:51 +0000 https://yetenaweg.com/?p=2907 አመታዊ የጤና ምርመራ በተለያየ የዕድሜ ክልል ላይ ላሉ ሰዎች የሚደረግ እና ለአንድ በሽታ የመጋለጥ
እድላቸውን ቀድሞ ለማወቅ የሚያስችል የምርመራ ዘዴ ነው።
እድሜ እና ፃታን መሠረት አድርገው በየአመቱ እና ከዛም በላይ ሊደረጉ የሚገቡ የምርመራ አይነቶች አሉ።
እነዚህን ምርመራዎች መረዳት እና መቼ መጠየቅ እንዳለቦት ማወቅ ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ ያግዝዎታል።
እንደ ካንሰር እና አንዳንድ በቅድመ ጥንቃቄ ልንከላከላቸው የምንችላቸውን ህመሞች ለመቆጣጠር ቀደም
ብሎ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።
ጤናማ በሚሆኑበት ጊዜ ምን ዓይነት ምርመራዎችን ማድረግ አለብዎት? ምን ዓይነት ምርመራዎችስ ሃኪምዎ
ሊይዝሎት ይችላል?

እድሜዎ ከ 18- 39 አመት ከሆነ

በዚህ እድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች አብዛኛውን ጊዜ በትምህርት፣ በስራ እና ቤተሰብን በማስተዳደር
የተጠመዱ በመሆናቸው አመታዊ የጤና ምርመራዎች ብዙ ጊዜ ሳይደረጉ ያልፋሉ።
● ክብደት እና ቁመት
● የደም ግፊት ልኬት
● የዓይን ምርመራ
● የጆሮ ምርመራ
● አጠቃላይ የደም ህዋሶች ምርመራ
● መሰረታዊ ወይም የተሟላ የሜታቦሊክ ፓነል (የኩላሊት አሰራር፣ የጉበት አሰራር ምርመራዎች፣
የተለያዩ የደም ውስጥ ንጥረ ነገሮች ምርመራ)
● የኮሌስትሮል ፍተሻ፡- HDL እና LDL ኮሌስትሮል
● የታይሮይድ ሆርሞን ምርመራ
● የስኳር በሽታ ምርመራ፡
● በ ደም ንክኪና በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች፡- ኤችአይቪ (HIV)፣ HPV፣
ጨብጥ፣ቂጥኝ ወይም ሌሎች ኢንፌክሽኖችን ሊያካትት ይችላል።
● የሽንት ምርመራ
● የልብ ምርመራ
● የሆድ አልትራሳውንድ
ለሴቶች ተጨማሪ ምርመራዎች
● የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ፡ በየ 3 አመቱ የፓፕ ስሚር ምርመራ ያደርጋል (ከ21 ዓመት ዕድሜ
ወይም ግንኙነት ማድረግ ከተጀመረበት ከ3 ዓመታት ጀምሮ)።

እድሜዎ ከ 40 አመት በላይ ከሆነ

በዚህ እድሜ ለተለያዩ በሽታዎች የመጋለጥ እድልዎ ይጨምራል። ስለዚህ ሃኪምዎ አመታዊ የሕክምና
ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። ይህም ጠቃሚ መረጃ የሚሰጡ ተጨማሪ ምርመራዎችን ማለፍ
ይጠይቃል።
● ክብደት እና ቁመት
● የደም ግፊት ልኬት
● የዓይን ምርመራ
● የጆሮ ምርመራ
● አጠቃላይ የደም ህዋሶች ምርመራ
● መሰረታዊ ወይም የተሟላ የሜታቦሊክ ፓነል (የኩላሊት አሰራር፣ የጉበት አሰራር ምርመራዎች፣
የተለያዩ የደም ውስጥ ንጥረ ነገሮች ምርመራ)

● የኮሌስትሮል ፍተሻ፡- HDL እና LDL ኮሌስትሮል
● የታይሮይድ ሆርሞን ምርመራ
● የስኳር በሽታ ምርመራ፡
● በጾታዊ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ምርመራ
● የሽንት ምርመራ
● የልብ ምርመራ
● የሆድ አልትራሳውንድ
● ኮሎኖስኮፒ: ከ50ዓመት ዕድሜ በኋላ (ከዚያ በታች ላሉ በሕክምና ታሪክ ላይ በመመስረት
ሊያስፈልግ ይችላል)
ለሴቶች ተጨማሪ ምርመራዎች
● ማሞግራም
● የኦስቲዮፖሮሲስ ምርመራ (Bone mineral density testing)፡- እድሜያቸው 65 እና ከዛ በላይ
ለሆኑ ሴቶች
● የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ
ለወንዶች ተጨማሪ ምርመራዎች
● የፕሮስቴት እና የፕሮስቴት ካንሰር ምርመራ፡ ዕድሜው 50 እና ከዚያ በላይ የሆኑ

Reference:
– Complete Guide to Annual Health Screenings by Age | Columbia NPG
(columbianps.org)
– 2020 Adult Preventive Health Guidelines

]]>
የወር አበባ ንፅህና አጠባበቅ https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%8a%95%e1%8d%85%e1%88%85%e1%8a%93-%e1%8a%a0%e1%8c%a0%e1%89%a3%e1%89%a0%e1%89%85/ Tue, 26 Jul 2022 03:55:08 +0000 https://yetenaweg.com/?p=2889  ለልቱ መገርሳ (በአ.አ.ዩ ህ/ጤ/ሳ/ኮ የ 4ኛ አመት የህክምና ተማሪ) 

በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ ሴቶች መካከል 52 በመቶ የሚሆኑት በየወሩ የወር አበባን ያያሉ፡፡ ነገር ግን ትክክለኛ የወር አበባ ንፅህና አጠባበቅ መረጃ ያላቸው ሴቶች ቁጥር በተለይ በታዳጊ ሀገራት አነስተኛ ነው። ዩኒሴፍ ዋሽ (UNICEF WASH) እኤአ ግንቦት 2017 በስድስት የኢትዮጵያ ክልሎች ባደረገው ሀገራዊ መሰረታዊ ጥናት መሰረት በጉርምስና ዕድሜ ላይ ከሚገኙ ልጃገረዶች መካከል የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ በ24 ሰዓታት ውስጥ  ከሶስት እስከ አራት ጊዜ መቀየር እንዳለበት የሚያውቁት 23.7%  ሴቶች ብቻ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ 11 በመቶ የሚሆኑ ልጃገረዶች የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ የሚቀይሩት በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ይህም የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው የወር አበባ ንፅህና አጠባበቅ መስፈርት መሰረት በቂ የሚባል አይደለም:: 

የወር አበባ ጤና እና ንፅህና የወር አበባን ከጤና ፣ ከደህንነት ፣ ከፍትሃዊነት ፣ ከጾታ እኩልነት እና ከትምህርት ጋር የሚያገናኙትን ሰፋ ያሉ የስርዓተ-ፆታ ሁኔታዎችን ያጠቃልላል። የዓለም ጤና ድርጅት (ዩኒሴፍ የጋራ ክትትል ፕሮግራም) በቂ እና ትክክለኛ የወር አበባ ንፅህና አጠባበቅን እንደሚከተለው ገልጿል፡-  ‘ሴቶች እና ልጃገረዶች የወር አበባን ደም ለመያዝ የሚያገለግል ንፁህ የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ መጠቀም ፣ በአሻቸው ጊዜ ግላዊነቱ በተጠበቀ ቦታ መቀየር ፣ በወር አበባ ጊዜ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሰውነትን ለማጠብ ሳሙና እና ውሃ መጠቀም ፣ ያገለገሉ የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለማስወገድ አስተማማኝ እና ምቹ መገልገያዎችን ማግኘት ፣ ከወር አበባ ዑደት ጋር የተቆራኙትን መሰረታዊ እውነታዎች መረዳት እና እንዴት በክብር ፣ በምቾት እና ያለፍራቻ የወር አበባ ንፅህናን መጠበቅ እንደሚቻል መገንዘብን ያካትታል።’

የወር አበባ ደም ለመያዝ የሚያገለግሉ የወር አበባ ቁሳቁሶች የንፅህና መጠበቂያ ፓድ፣ ጨርቆች፣ ታምፖኖች እና  የወር አበባ ካፕስን ያካትታሉ። የወር አበባ ንፅህና አጠባበቅን ከሚደግፉ እቃዎች መካከል የአካል እና የልብስ ማጠቢያ ሳሙና፣ የውስጥ ሱሪ ፣ የህመም ማስታገሻ መድሀኒቶች እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ።

 

ትክክለኛ የወር አበባ ጤና እና የንጽህና አጠባበቅ ልምዶች የሚከተሉትን ይመስላሉ፡-

 

በቀን ቢያንስ ከ 3 እስከ 4 ጊዜ (በየ 4-6 ሰአታት) የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ መቀየር አለበት። የውስጥ ልብሶች በየጊዜው እንደየአስፈላጊነቱ መለወጥ አለባቸው።

አንድ የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ እርጥብ ከሆነ ወዲያውኑ መቀየር አለበት።

በወር አበባ ወቅት የቀረውን ደም ለማስወገድ ውጫዊው የብልት አካል መታጠብ አለበት።

ሴቶች የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ከመቀየራቸው በፊት ሁልጊዜም እጃቸውን በሳሙና መታጠብ አለባቸው።

ብልታቸውን ከፊት ወደ ኋላ ብቻ በመታጠብ እና ፊንጢጣና ብልትን ባለማነካካት ከፊንጢጣ ወደ ብልት በሚመጣ ባክቴሪያ የሚፈጠር ኢንፌክሽንን መከላከል ይገባቸዋል።ብልትን በሚታጠቡ ጊዜ በጣም ጥሩው አማራጭ ውሃ ብቻ መጠቀም ነው።

ያስተውሉ!

በቂ እና ትክክለኛ ያልሆነ የወር አበባ ንፅህና አጠባበቅ እንደ የሽንት ቧንቧ ላሉ ኢንፌክሽኖች ተጋላጭ ያደርጋል። ይህም ወደፊት መካንነት እና ከወሊድ ጋር የተገናኙ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።

ማጣቀሻ

  1. Guidance for monitoring menstrual health and hygiene (version 1) June 2020 UNICEF
  2. Menstrual hygiene Management Training module, UNICEF Maharashtra, 2014
  3. Menstrual Health Education Resource Second edition, 2013
  4. Menstrual Hygiene Management In Ethiopia National Baseline Report from Six Regions of Ethiopia UNICEF WASH May 2017

 

]]>
የወር አበባ ዑደት (Menstrual Cycle) https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%8b%91%e1%8b%b0%e1%89%b5-menstrual-cycle/ Mon, 18 Jul 2022 18:22:16 +0000 https://yetenaweg.com/?p=2884 በእምነት የሻው በቅ/ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የ5ኛ ዓመት የህክምና ተማሪ

የወር አበባ ዑደት የምንለው የወር አበባ ከጀመረበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቀጥለው የወር አበባ እስከሚጀምርበት የመጀመሪያው ቀን ያለውን ነው፡፡

የወር አበባ ዑደት ዋና ተግባር በእንቁልጢ (የእንቁላል እጢ) ዉስጥ ከሚገኙት ያልበሰሉ እንቁላሎች በየወሩ (በየ 28 ቀኑ) አንዱን መርጦ በማብሰል ምናልባት የወንድ ዘር ፍሬ ወደ ማህፀን ቢገባ ፅንስ እንዲፈጠር ዝግጁ ለማድረግ ነዉ፡፡ ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቢቀር ከማህፀን የሚፈስ ደም ሆኖ ወደ ዉጪ ይወጣል፡፡ ይህንንም የወር አበባ እንለዋለን፡፡ መደበኛዉ የወር አበባ ዑደት ከ 21 እስከ 35 ቀን ሲሆን የጊዜው ርዝመት እንደየሴቶቹ ይለያያል፡፡ ነገር ግን በአማካኝ 28 ቀንን መዉሰድ እንችላለን፡፡ 

የወር አበባ ዑደት ላይ ምን ይፈጠራል?

በእያንዳንዱ ዑደት መጀመሪያ ላይ ከሴቲቱ  እንቁልጢ ዉስጥ ለጋ እንቁላሎች ተመርጠዉ ወደ ብስል እንቁላልነት ያድጋሉ በዚህ ጊዜ በበሰሉት እንቁላሎች ዙሪያ ያለው ሽፋን ኤስትሮጅን የሚባለዉን ሆርሞን ያመነጫል፡፡  በእነዚህ የበሰሉ እንቁላሎች የሚመነጨው ኤስትሮጅን ወደ ማፀን ይሄድና የማህፀን የዉስጥ ግድግዳ እንዲወፍር ትዕዛዝ ይሰጠዋል፡፡ የማህፀን ዉስጣዊ ግድግዳ ይህን ትእዛዝ በመቀበል ቀድሞ ከነበረዉ ዉፍረት ይጨምራል፡፡

ይህንን ሂደት በ28 ቀን ዑደት ምስል ላይ ስናሰፍረዉ ከአንድ እስከ አስራ አራት ያለዉን ቀን ይይዛል፡፡

 

ቀን 1 _____↔________ቀን 14   _____________   ቀን 28 

 

ስለዚህ በአስራ አራተኛዉ ቀን በእንቁልጢ ዉስጥ ጥቂት የበሰሉ እንቁላሎች ሲኖሩ በማህፀን ዉስጥ ደግሞ ዉስጣዊ ግድግዳዉ ወፍሮ ተዘጋጅቷል ማለት ነዉ፡፡ በዚህ ጊዜ አብዛኞቹ እንቁላሎች ይሞቱ እና አንዱ ብቻ ይቀራል፡፡

በወር አበባ ዑደት መካከል ላይ (አጋማሽ ላይ) ማለትም በ14ኛዉ ቀን አካባቢ የሚከተሉት ለውጦች ይደረጋሉ፡፡

  • እንቁላሉ ከእንቁልጢ በመዉጣት በአስተላላፊ ቱቦ (Fallopian tube) በኩል አድረጎ ወደ ማህፀን አቅጣጫ መሄድ ይጀምራል፡፡
  • እንቁልጢ ፕሮጀስትሮን ሚባል ሆርሞን ማምረት ይጀምራል፡፡  

 

ይህ ፕሮጂስትሮን የሚባለዉ ሆርሞን ወደ ማህፀን በመሄድ ቀድሞ ወፍሮ የነበረዉን ግድግዳ በደምስሮች እና በእጢዎች እንዲበለፅግ ያደርገዋል፡፡ የዚህ ሁሉ የማህፀን ግድግዳ መዘጋጀት ዓላማዉ  ዕንቁላሉ ከወንዴ ዘር ጋር ቢገናኝ (ሴቲቱ ሩካቤ ብትፈፅም) በዚህ የማህፀን ግድግዳ ላይ ተጣብቆ ወደ ፅንስነት ማደግ እንዲችል ነዉ፡፡

 

  ይህንን ሂደት በ28 ቀን ዑደት ምስል ላይ ስናሰፍረዉ ከ14ኛዉ ቀን በኋላ ያለዉን ይይዛል፡፡

 

ቀን 1 ____________ቀን 14______↔__________   ቀን 28

በወር አበባ ዑደት ውስ ካሉት ቀናት መካከል በዚህ እንቁላሉ ሚለቀቅበት ጊዜ ግንኙነት ቢፈጸም እርግዝና የመፈጠር እድሉ ሰፊ ይሆናል፡፡ ይህም ብዙ ጊዜ ከሚቀጥለው የወር አበባ 12 እስከ 14 ቀን በፊት ያሉትን ቀናት ይመለከታል፡፡

የበሰለው እንቁላል ከተለቀቀበት ጊዜ አንስቶ ላሉት 2ቀናት ይቆይና ወንዴ ዘር ካልመጣና ካልተገናዉ ይሞታል፡፡ ይህ በአስተላላፊ ቱቦዎች ዉስጥ እያለ የሞተዉ እንቁላል በሰዉነታችን ነጭ የደም ህዋሳት ይበላል፡፡  በመጨረሻም እንቁልጢው ፅንስ ባለመፈጠሩ ምክንያት ፕሮጅስትሮን ማምረቱን ያቆማል፡፡ በዚህ ጊዜ ወፍሮና በደምስር በልጎ የነበረዉ ዉስጣዊ የማህፀን ግድግዳ ይሸረሽርና ከደም ጋር ይወጣል፡፡ ሴቲቱም የወር አበባ ይኖራታል ማለት ነዉ፡፡ ይህ ሁኔታ ለአምስት ቀናት አካባቢ ይቀጥላል፡፡ በጤነኛ ሴቶች ላይ ከ 20 እስከ 80 ሚሊ ሊትር ያህል ደም ይፈሳል፡፡    

   ይህ ሁሉ ባይሆን እና የወንዴ ዘር ከእንቁላል ጋር ቢገናኝ ግን ውሕደት (Fertilization) ይከሰታል፡፡ የተዘጋጀዉ የማህፀን ግድግዳ ላይም በሂደት የዳበረዉ እንቁላል ተጣብቆ ወደ ፅንስ እድገት ያመራል፡፡ የማህፀኑ ዉስጣዊ ግድግዳም አስፈላጊ በመሆኑ እንደበፊቱ የሚሸረሸር አይሆንም፤ ፕሮጅስትሮንም መመረቱን ይቀጥላል፡፡ በዑደቱ መጨረሻ ላይም ደም መፍሰሱ ይቀራል ማለት ነዉ፡፡ የወር አበባ መጥፋት የእርግዝና የመጀመሪያ ምልክት የሆነበትም ምክንያት በዚህ ነዉ፡፡

 

]]>
የመጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%aa%e1%8b%ab%e1%8b%8e%e1%89%b9-1000-%e1%89%80%e1%8a%93%e1%89%b5/ Thu, 03 Feb 2022 09:27:30 +0000 https://yetenaweg.com/?p=2613 (በፍሰሀ ሙሉጌታ Myungsung Medical college የህክምና ተማሪ-C1)

የመጀመሪያዎቹ 1000 የህይወት ቀናት ማለት በሴት ልጅ እርግዝና እና በልጇ ሁለተኛ    ልደት መካከል ያሉት ቀናቶች ናቸው፡፡   ይህም ጊዜ  ለሙሉ ጤና እና እድገት መሠረት  የሆነ   ነው።          በዚህ ጊዜ ውስጥ የልጁ አመጋገብ እና እንክብካቤ ህይወቱን ጤናውን ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን በልጁ  እድገት እና የመማር ችሎታ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ በዚህ ጊዜ አእምሯችን ከሌሎች ዕድሜ ክልሎች በበለጠ ፍጥነት ያድጋል። ስለዚህ ለልጁ ተገቢውን ንጥረ ነገር መመገብ በጣም አስፈላጊ ነው::

የመጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት በ 3 ይከፋላሉ:-

1. የእርግዝና ጊዜ (0-9 ወር)

2. Infant (0-1 አመት)

3. Toddler (1-2 አመት)

1,የእርግዝና ጊዜ (0-9 ወር)

በእርግዝና ወቅት አዕምሮ በፍጥነት ማደግ ይጀምራል:: በእርግዝና የመጀመሪያ ወር መጨረሻ ላይ ፅንሱ 10,000 ነርቮች እንዳሉት ይገመታል፣በ 6ተኛው ወር መጨረሻ 10 ሚሊዮን ይደርሳል።፡ በዚህ ጊዜ ፅንሱ ከእናቱ የሚያገኘው ንጥረ ነገሮች  ነርቮቹን የመፍጠር ሂደት ላይ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በዋነኝነት  አይረን፣ፕሮቲን፣ኮፐር፣ ፎሌት፣ ዚንክ ፣ አዮዲን እና ቅባቶች ናቸው፡፡ እነዚህንም ለማግኘት የሚከተሉትን ምግቦች ቢመገቡ ይመረጣል፡-

1. አትክልቶች እና ፍራፍሬዎች

2. ሥጋ

3. ምስር

4. አቮካዶ

5. የዱባ ፍሬ

6. የወተት ምርቶች

7. ስፒናች

8. ሰላጣ

9. ስኳር ድንች

በተቃራኒው እርግዝና ወቅት ከሚከተሉት ምግቦች መራቅ ይመከራል:-

1. ቱና እና ማርሊንን ጨምሮ ከፍተኛ የሜርኩሪ ዓሳን ያስወግዱ።

2. ያልበሰል ስጋ፣እንቁላል

3. ምንም እንኳን ጉበት ስጋ ጥሩ የቫይታሚን ኤ፣ቫይታሚን ቢ12፣ እና ፎሌት ምንጭ ነገር ግን ከመጠን በላይ ቫይታሚን ኤ መመገብ ፅንሱን ሊጎዳ ይችላል። ስለዚህ የሚበላውን መጠን ይገድቡ ፡፡

4.ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ቶክሶፕላዝሞሲስ በተባሉ ተውሳኮች ሊበከሉ ይችላሉ፡፡ ሁሉንም ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን በንጹህ ውሃ ማጠብ አስፈላጊ ነው፡፡

5. ሁሉንም የአልኮል ዓይነት ያስወግዱ፡፡ አልኮል መጠጣት የፅንስ መጨንገፍ እና የአእምሮ ዘገምተኝነትን ያስከትላል፡፡

2, Infant (0-1 አመት)

ሕፃን ልጅ ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ እስከ አንድ አመት ድረስ ያለው ጊዜ ነው፡፡ ልክ በእርግዝና ጊዜ አመጋገብ ትልቅ ሚና እንደሚጫወተው በዚህም ጊዜ ወሳኝ ነው፡፡

ልጁ በዚህ ጊዜ ሊወስዳቸው ከሚገባቸው ምግቦች አንዱ እና ዋነኛው የጡት ወተት ነው፡፡ የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና ማህበር ለመጀመሪዎቹ 6 ወራት ጡት ማጥባት ብቻ ያለ ምንም ተጨማሪ ምግብ እና መጠጥ ይመከራል፡፡ ከዚያም በተጨማሪ ለ 1 አመት ያህል ከምግብ እና ፈሳሽ ጋር ጡት ማጥባት ተገቢ ነው፡፡  በቀን እስከ 20 ጊዜ ጠዋት እና ማታ ያጥቡ፡፡

 

ጡት ማጥባት ህፃኑን ብቻ ሳይሆን የሚጠቅመው እናቶችንም ከጡት እና ከማህፀን ካንሰር ለመከላከል ይረዳል፡፡

ምግብ ሲጀምሩ የሚከተሉትን ነገሮች አስተውሉ፡-

1. በመጀመሪያ አንደኛውን ጡት ሙሉ በሙሉ ባዶ ማድረግ ከዚያም ወደሌላኛው ጡት ይሂዱ። ይሄ ህፃኑ የሚቻለውን ያህል ንጥረነገር እንዲያገኝ ያግዛል፡፡

2. ልጅዎ ቢታመም በቀን የሚጠባበትን ቁጥር ይጨምሩ፡፡

3. ከወሊድ በኋላ ባሉት 45 ቀናት ውስጥ የቫይታሚን ኤ ታብሌቶች ወይም ምግቦችን ይውሰዱ፡፡

4. ልጅዎን በቀን ከ20-30 ደቂቃዎች የፀሀይ ብርሀን ያሙቁ፡፡

5. ምግብ በሚጀምሩበት ጊዜ ለልጅዎ በአንድ ጊዜ አንድ አዲስ ምግብ ብቻ ይስጡት – ድብልቅ ሳይሆን (እንደ ጥራጥሬ እና ፍራፍሬ ወይም ስጋ)። ሌላ አዲስ  ምግብ ከመጨመርዎ በፊት አዲሱን ምግብ ከ 3 እስከ 5 ቀናት በተከታታይ ይስጡት፡፡ በዚህ መንገድ ልጅዎ ለምን አይነት ምግቦች አለርጂክ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማወቅ ይችላሉ።

6. በትንሽ መጠን አዲስ ምግብ ይጀምሩ – መጀመሪያ ላይ አንድ የሻይ ማንኪያ እና ቀስ በቀስ ወደ አንድ የሾርባ ማንኪያ ከፍ ያድርጉ።

7. በደረቅ የሩዝ እህል ይጀምሩ ከዛ አትክልቶች ፣ ፍራፍሬዎች እና ከዚያም ስጋዎች ይመገቡ፡፡

8. በቤት ውስጥ የተሰሩ የህጻናት ምግቦችን በምታዘጋጁበት ጊዜ ጨው ወይም ስኳርን አይጠቀሙ፡፡ የታሸጉ ምግቦች ከፍተኛ መጠን ያለው ጨው እና ስኳር ሊይዙ ስለሚችሉ ለህጻናት ምግብ መዋል የለባቸውም። ለተገቢ ያልሆነ ውፍረት ያጋልጣሉ፡፡

9. የላም ወተት ከ1 አመት በፊት መጀመር የለበትም፡፡

10. ሁልጊዜ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ይጠቡ፣ ይላጡ እና ፍሬውን ያስወግዱ።

11. ከመሬት ጋር የሚገናኙ ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶች እና ማር ላይ ልዩ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡ የምግብ መመረዝን የሚያስከትሉ የ ቦቱሊዝም(botulism) ንጥረ ነገሮችን ሊይዙ ይችላሉ፡፡ እስከ 1 አመት ድረስ ልጆች ማር መመገብ የለባቸውም፡፡

 

3,Toddler (1-2 አመት)

ህፃናት ልጆች እንዲያድጉ እና ተገቢ የሆነ የክብደት መጠን እንዲያገኙ  በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦችን ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ስንዴ፣ ስኳር የሌለው ወተት እና ሌሎች የወተት ተዋጽኦዎች ያስፈልጋቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ የቅባት እና የስኳር መጠንን መመጠን አስፈላጊ ነው፡፡ የክብደት መጠን መጨመር በወደፊት ህይወት ላይ ለአላስፈላጊ በሽታዎች ይዳርጋል፡፡

የልጆች ባህሪን ለመቆጣጠር ምግብን ከመጠቀም ይልቅ የራሳቸውን ምግብ መጠን እንዲቆጣጠሩ መፍቀድ ይመከራል። ልጆች ወላጆቻቸውን እና ሞግዚታቸውን ይመለከታሉ፡፡ ስለዚህ አንድ ወላጅ ጤናማ ምግብ ሲመገብ ልጆቹም እንዲመገቡ ያነሳሳቸዋል።

ልጅዎ በቀን ግማሽ ሊትር ወተት ማግኘት አለበት፡፡ ይህም በቂ ካልሺየም፣ ቫይታሚን ዲ እና ስብ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

1. ልጅዎ ከሁሉም የምግብ ዓይነቶች ማለትም ከአትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች፣ ፕሮቲኖች፣ ጥራጥሬዎች እና የወተት ተዋጽኦዎች ምግብ ማግኘት አለበት።

2. ልጅዎን ጡጦ ሳይሆን ኩባያ እንዲጠቀም ያበረታቱት።

3. ሹካ/ማንኪያ መጠቀምን ጨምሮ የጠረጴዛ ስነምግባርን ማስተማር መጀምር

4. ታገሱ! ህፃናት አንድን ነገር አንድ ቀን መውደድ እና በሚቀጥለው ጊዜ መብላት እንደማይፈልጉ በመወሰን መራጭ ተመጋቢዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ከሁሉም     ምግቦች ትንሽ ክፍሎች ያቅርቡ እና የምግብ ሰዓቱን አስደሳች ያድርጉት! የተለያየ ጣዕም ያላቸው ባለቀለም ምግቦችን ያቅርቡ። ዛሬ ምግብን እምቢ ቢሉም     ማገልገልዎን ይቀጥሉ እና እንዲሞክሩ ያበረታቷቸው፤ነገር ግን እንዲበሉ አያስገድዷቸው፡፡

5. መላው ቤተሰብ አንድ ላይ ቢመገብ ፤አንድ አይነት ምግብ ይመገቡ፤ በዚህ ተነሳስቶ ህጻኑም ተመሳሳይ ምግብ ይመገባል፡፡

6. ለልጅዎ በቀን ሶስት መደበኛ ምግቦች እና 2 መክሰስ ያቅርቡ፡፡

References

1. American Academy of Pediatrics

2. NUTRITION IN THE FIRST 1,000 DAYS: A Foundation for Brain Development and Learning. (n.d.).     Retrieved from https://thousanddays.org/.

3. Health, F. D. (2006). Complementary Feeding Recipes for Ethiopian Children 6-23 Months Old.

  • https://www.stanfordchildrens.org/en/topic/default?id=feeding-guide-for-the-first-year-90-P02209. (n.d.). Retrieved from https://www.stanfordchildrens.org.

 

ይህ ፅሁፍ በዶ/ር ትንሳኤ አለማየሁ (የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት/የተላላፊ በሽታዎች ሰብ ስፔሻሊስት) እና የጤና ወግ ኤዲተሮች የተገመገመ ነው።

]]>
የእናቶች ሞት በኢትዮጵያ https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a5%e1%8a%93%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%88%9e%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab/ Thu, 03 Feb 2022 08:54:02 +0000 https://yetenaweg.com/?p=2598 በሁስኒያ አደም (ጎንደር ዩ/ህ/ጤ/ሳ/ኮ የህክምና ተማሪ-C2)

A mother with her newborn child at Dessie Referral Hospital in Afar region, Ethiopia. Save the Children staff refer girls and women with health problems from rural Amhara to the hospital and assist them in their journey there.

በእያንዳንዱ ቀን ከ2 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማስቀረት በምንችላቸው ከእርግዝና እና ወሊድ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች የሴት ልጅ ህይወት እንደሚያልፍ ያውቃሉን?

እ.ኤ.አ. በ2017 የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው 295,000 የሚሆኑ ሴቶች በእርግዝና እና ወሊድ ወቅት ህይወታቸው አልፏል። ከዚህም ውስጥ 94% የሚገኙት እያደጉ ባሉ ሀገራት ውስጥ ነው። ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ብቻ 66% (196,000) የእናቶች ሞት ሲመዘገብ፣ ኢትዮጵያ 5% (14,000) ትይዛለች።

የእናቶች ሞት ማለት ምን ማለት ነው?

የእናቶች ሞት ማለት በእርግዝና ጊዜ ወይም ከወሊድ በኋላ በመጀመሪያ 42 ቀናቶች ውስጥ ከእርግዝናው ጋር ተያይዘው በሚመጡ የጤና ችግሮች ወይም በእርግዝናው ምክንያት ሊባባሱ በሚችሉ እና በህክምና አገልግሎት ችግር የሚከሰቱ የሴት ልጅ ሞት ማለት ነው።

በእርግዝና እና ወሊድ ጊዜ የሚከሰቱትን የጤና ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችሉ መፍትሄዎች በመኖራቸው አብዛኛውን የእናቶች ሞት መከላከል ይቻላል። በዋነኝነት ሁሉም የወሊድ አገልግሎት በትክክለኛ ጊዜ እንዲሁም ብቁ በሆኑ የጤና ባለሙያዎች መሰጠት አለበት። ይህም የአንድን እናት እንዲሁም የልጇን መኖር አለመኖር ይወስናል።

ለእናቶች ሞት የሚዳርጉ መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

አብዛኛዎቹ የጤና ችግሮች በእርግዝና ወቅት የሚመጡ ሲሆኑ የቀሩት ከእርግዝና በፊት በነበሩ የጤና ችግሮች በእርግዝናው ምክንያት በመባባሳቸው የሚመጡ ናቸው።

ከባድ የደም መፍሰስ (በአብዛኛው ከወሊድ በኋላ የሚፈሰው ደም) ፣ በእርግዝና ወቅት የደም ግፊት መጨመር (pre-eclampsia and eclampsia) ፣ ኢንፌክሽን (sepsis) ፣ ከባድ ምጥ (Obstructed labour) እንዲሁም ከጤና ተቋም ውጪ ፣ ብቁ ባልሆኑ ባለሙያዎች እና በህክምና መሳርያ ያልታገዘ ውርጃ (Unsafe abortion) ለእናቶች ህይወት ማለፍ ዋነኛ መንስኤ ተደርገው ይወሰዳሉ።

የህክምና አገልግሎትን ለማግኘት ውሳኔን ማዘግየት ፣ ወደ ህክምና ተቋም ለመድረስ መዘግየት እና የጤና ተቋም ከደረሱ በኋላ አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ሳያገኙ መዘግየት የእናቶችን ሞት የሚያስከትሉ ሶስቱ የመዘግየት ሞዴል (The Three Delays Model) በመባል ይታወቃሉ።

የእናቶች ሞት መጠን በእናቶች የእድሜ ክልል ይለያያል። በ 10 – 14 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣት ልጃገረዶች በእርግዝና እና ወሊድ ምክንያት ከሌሎች የእድሜ ክልሎች በበለጠ ለሞት ይዳረጋሉ።

የእናቶችን ሞት እንዴት ማስቀረት እንችላለን?

. የአለም ጤና ድርጅት እንደሚያመለክተው የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት የእናቶችን ሞት በመቀነስ ዙሪያ ጉልህ ሚና ይጫወታል። ይህም ያልተፈለገ እርግዝናን በማስቀረት ከእርግዝና  እና      ውርጃ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የእናቶችን ሞት ይቀንሳል። የአፍላ እድሜን እርግዝና በማዘግየት የወጣት ልጃገረድን ህይወት ይታደጋል። በተጨማሪም የልጆቻቸውን ቁጥር፣ መች እና     በምን ያህል ርቀት እንደሚወልዱ ለማቀድ ያስችላል።

. የቅድመ ወሊድ ክትትል አገልግሎት ጤናማ የእርግዝና ጊዜን ለማሳለፍ ሌላኛው መፍትሄ ነው።

. የቅድመ ወሊድ ክትትል አገልግሎት ብቻውን በቂ አይሆንም። የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ጤናማ የእርግዝና ጊዜ ማሳለፍ አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ በወሊድ ወቅትም በጤና ተቋም ብቁ ባለሙያ ባለበት መሆኑ አስፈላጊ ነው።

በሀገራችንም ባለፉት 15 አመታት ውስጥ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት የሚጠቀሙ እናቶች መጠን በ27% ፣ የቅድመ ወሊድ ክትትል ያላቸው በ56% እንዲሁም በጤና ተቋም የወሊድ አገልግሎት ያገኙ በ22% መሻሻል አሳይቷል።

ከ1990 – 2015 የእናቶች ሞት መጠን ለውጥ ቢያሳይም አጥጋቢ አልነበረም። ውጤቱም ኢትዮጵያ ከምዕተ አመቱ የልማት ግቦች (MDGs) ጋር በተያያዘ ከታቀደው በታች መሆኑን ያሳያል።

በ2030ም EPMM (Ending Preventable Maternal Mortality) በእያንዳንዱ ሀገራት የሚከሰተውን የእናቶችን ሞት ቢያንስ በሁለት ሶስተኛ (2010ን መነሻ በማድረግ) ለመቀነስ ግብ አስቀምጧል።

 

ማጣቀሻ

  1. Ethiopian Public Health Institute (EPHI) and ICF. 2021. Ethiopia Mini Demographic and Health Survey 2019: Final Report. Rockville, Maryland, USA: EPHI and ICF.
  2. Organization WH. 2015. Strategies towards ending preventable maternal mortality (EPMM).
  3. Organization WH. 2019. Trends in maternal mortality 2000 to 2017: estimates by WHO, UNICEF, UNFPA, World Bank Group and the United Nations Population Division.
  4. Say L, Chou D, Gemmill A, Tunçalp Ö, Moller A-B, Daniels J, et al. 2014. Global causes of maternal death: a WHO systematic analysis. The Lancet global health. 2(6):e323-e33.
  5. Tessema GA, Laurence CO, Melaku YA, Misganaw A, Woldie SA, Hiruye A, et al. 2017. Trends and causes of maternal mortality in Ethiopia during 1990–2013: findings from the Global Burden of Diseases study 2013. BMC public health. 17(1):1-8.

ይህ ፅሁፍ በዶ/ር ዳዊት ወርቁ (የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስ/የማህፀን ካንሰር ሰብ ስፔሻሊስት) እና የጤና ወግ ኤዲተሮች የተገመገመ ነው።

 

]]>
የማህፀን ጫፍ ካንሰር በኢትዮጵያ https://srhr.yetenaweg.com/%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%88%85%e1%8d%80%e1%8a%95-%e1%8c%ab%e1%8d%8d-%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab/ Thu, 13 Jan 2022 14:44:21 +0000 https://yetenaweg.com/?p=2470 በቤቴልሄም መኮነን (በጎንደር ዩኒቨርሲቲ /// የህክምና ተማሪ-C2)

አብዛኞቻችን ካንሰር የሚለውን ስም በሀገራችን መስማት ከጀመርን ሩቅ አይደለም፡፡ በተለይም በገጠሩ የሀገራችን ማህበረሰብ ዘንድ ገና በመታወቅ ላይ ያለ ህመም ነው፡፡ በዚህም የተነሳ መታከም እንደሚችል ከማሰብ ይልቅ የፈጣሪ ቁጣ እንደሆነ የሚያስቡም በርካቶች ናቸው፡፡

በሀገራችን በርካታ ጥናቶች ባይደረጉም፣ ካንሰር 5.8 ከመቶ አመታዊ የሞት ምጣኔ እንዳለው ይገመታል፡፡ በስፋት ተሰራጭተው ከሚገኙት መካከል የጡት ካንሰር 30.2ከመቶ የሚሆነውን ድርሻ ሲይዝ የማህፀን ጫፍ ካንሰር 13.4ከመቶ እንዲሁም የትልቁ አንጀት ካንሰር 6.3ከመቶ የሚሆነውን ድርሻ በመያዝ ተቀምጧል፡፡

የማህፀን ጫፍ ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ ሌሎች ካንሰሮች በ4ኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል፡፡ እንደ የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ጥናት መሰረት በ2020 በመላው ዓለም ከ604,000 በላይ ሴቶች በዚህ ካንሰር የተጠቁ ሲሆኑ ከ342,000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በኢትዮጵያም ከ6,294 የካንሰሩ ተጠቂዎች 4,884 የሞት ሰለባዎች ሆነዋል፡፡

በ2019 የተደረገው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ አብዛኞቹ የካንሰሩ ተጠቂዎች ስለ ካንሰሩ ምንም እውቀት የሌላቸው ሲሆኑ ሲመረመሩም በስፋት ወደ ሰውነታቸው ከተሰራጨ በኋላ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሚታየው የግንዛቤ ማነስ ትኩረት የሚሻ ነው፡፡

የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምንድን ነው?

✓ መከላከል እንደሚቻል እንዲሁም ቢታከም መዳን እንደሚችል ያውቃሉ ?

✓ ይህ ካንሰር ማህፀን በር አካባቢ ያሉ ህዋሶቻችን ከመጠን በላይ ሲራቡ የሚፈጠር እጢ ነው፡፡

✓ ከሞላጎደል ሁሉም(99%) የማህፀን ጫፍ ካንሰሮች ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ (Human Papilloma Virus) በተሰኘ የቫይረስ ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው፡፡ ይህ ቫይረስ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በማድረግ የሚተላለፍ ነው፡፡ አንዲት ሴት በዚህ ቫይረስ (HPV) ብትጠቃም፣ ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የመዳን እድል አለው በተለይም ከ90ከመቶ በላይ በ2ዓመት ይድናል፡፡

በምን ምክንያት ወደ ካንሰር ሊለወጥ ይችላል?

➢ አንዲት ሴት ከ16 ዓመቷ በፊት ወሲብ መፈፀም ከጀመረች አልያም ደግሞ የወር አበባ ማየት በጀመረችበት ዓመት ወሲብ ከፈፀመች

➢ ከአንድ በላይ የወሲብ ጓደኞች ከነበሯት

➢ የሚዋጥ የወሊድ መቆጣጠሪያ የምትጠቀም ከሆነ በተለይም ለ5 ዓመትና ከዚያ በላይ ➢ ሲጋራ የምታጨስ ከሆነ

➢ የተዳከመ በሽታን የመቋቋም አቅም ካላት

➢ የምግብ ዕጥረት ለምሳሌ እንደ ቫይታሚን ቢ፣ሲ፣ኢ የመሳሰሉት

➢ በአባላዘር በሽታዎች ከተጠቃች

➢ የቅድመ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ አድርጋ የማታውቅ ከሆነ

➢ ዝቅተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ

ምልክቶቹ ምንድናቸው?

ከሆነ በአስቸካይ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ የሀኪም እርዳታ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ካንሰር ምንም ምልክት ላያሳይ ይችላል ወይም ደግሞ መጠነኛ ምልክቶች ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም መዘናጋት ተገቢ አይደለም፡፡

የማህፀን ጫፍ ካንሰርን እንዴት እንከላከል?

ቅድመ መከላከል

ለታዳጊ ሴቶች ማለትም ከ9-14ዓመት ለሆኑ

➢ የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ(HPV) ክትባት መስጠት

➢ በሀገራችንም እ.ኤ.አ ከ2018 ጀምሮ ከ14 ዓመት በላይ ለሆኑ ታዳጊዎች በየትምህርት ቤቱ እንዲሁም በጤና ተቋማት የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ(HPV) ክትባት መሰጠት ተጀምራል፡፡ይህ ተግባር ሁሉንም ዜጋ ተደራሽ በማድረግ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡

ለሴቶችና ለወንዶች

➢ እድሜና ባህልን መሰረት ያደረገ የጾታዊ ግንኙነት ትምህርት መስጠት

➢ ወሲብ መፈፀም ለጀመሩ ኮንዶምን እንዲጠቀሙ ማበረታታት

➢ የወንዶች ግርዛት

➢ ስለ ሲጋራ የጤና ጠንቆች ግንዛቤ መስጠት

2ኛ ደረጃ መከላከል

➢ 30ዓመትና ከዛ በላይ ለሆኑ ሴቶች የሚተገበር ሲሆን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የቅድመ ካንሰር ምርመራ ማድረግ ነው

3ኛ ደረጃ መከላከል

እንደአስፈላጊነቱ ለሁሉም ሴቶች ሲሆን በተለይም አደገኛ የሆኑትን የካንሰር ምልክቶች ማሳየት ለጀመሩ ሴቶች ተገቢውን ህክምና መስጠት ነው፡፡

አማራጮቹም ፡-

– የቀዶ ህክምና

– የጨረር ህክምና

– ኬሞቴራፒ

የአሜሪካ የካንሰር ማህበረሰብ፣ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራን በተመለከተ መቼ መጀመር እንዳበትና መች እንደሚቋረጥ የሚከተለውን ያስቀምጣል ፡

– አንዲት ሴት ወሲብ መፈፀም ከጀመረች ከ3ዓመት በኋላ፤ ከ21ዓመት ባይበልጥ ይመከራል

– እንደአስፈላጊነቱ በየ2 ወይም በ3 ዓመት ልዩነት መደገም አለበት፡፡ ይሁንእንጂ እንደ ኤች.አይ.ቪና ሌሎች በሽታን የመቋቋም አቅምን የሚያዳክሙ ሁኔታዎች ካሉ በየአመቱ መደገም እንዳለበት ተቀምጧል፡፡

– አንዲት ሴት ላለፉት 10ዓመታት ምንም አስጊ ሁኔታ ላይ ካልሆነች ከ70 ዓመቷ በኋላ የቅድመ ምርመራውን ማቋረጥ ትችላለች

ዋቢ

  1. Saleem A, Bekele A, Fitzpatrick MB, Mahmoud EA, Lin AW, Velasco HE, et al. Knowledge and awareness of cervical cancer in Southwestern Ethiopia is lacking: A descriptive analysis. PLoS One. 2019;14(11):e0215117.
  2. Begoihn M, Mathewos A, Aynalem A, Wondemagegnehu T, Moelle U, Gizaw M, et al. 2019. Cervical cancer in Ethiopia–predictors of advanced stage and prolonged time to diagnosis. Infectious agents and cancer, 14(1):1-7.
  3. world health organization.2021. Cervical cancer. https://www.who.int/health-topics/cervical cancer#tab=tab_1
  4. world health organization.2021. cervical cancer elimination initiatives. https://www.who.int/initiatives/cervical-cancer-elimination-initiative

 

ይህ ፅሁፍ በዶ/ር ዳዊት ወርቁ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት/የማህፀን ካንሰር ልዩ ስፔሻሊስት) እና የጤና ወግ ኤዲተሮች የተገመገመ ነው።

]]>